በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአለም ደረጃ ያሉት የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን ለመወጣት አለም መተባበር እንዳለበት የድርጅቱ ሃላፊ አሳስበዋል

ፋይል ፎቶ - የአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ሃላፊ ክሪስቲን ለጋርድ
ፋይል ፎቶ - የአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ሃላፊ ክሪስቲን ለጋርድ

“የእድገቱ ሁኔታ ከሚገባው በላይ ለረዘመ ጊዜ አዝግሞ ቆይቷል” ሲሉ ለጋርድ በፍራንክፈርት ጀርመን ባደረጉት ንግግር ጠቁመዋል። በበለጸጉት ሃገሮች የተንጸባረቁ ተግዳሮቶች ያልዋቸውን ዘርዝረዋል።

የአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ሃላፊ ክሪስቲን ለጋርድ በአለም ደረጃ ያሉት የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን ለመወጣት አለም መተባበር እንዳለበት አሳስበዋል። ተግዳሮቶቹ የእድገት ማዝገምን፣ የሸቀጣሸቀት ዋጋ መውረድንና ብዙ መንግስታት ሊያካሄዱት የሚችሉ የገንዘብ ትግል ያሉትን እንደሚያካትት ገልጸዋል።

“የእድገቱ ሁኔታ ከሚገባው በላይ ለረዘመ ጊዜ አዝግሞ ቆይቷል” ሲሉ ለጋርድ በፍራንክፈርት ጀርመን ባደረጉት ንግግር ጠቁመዋል። በበለጸጉት ሃገሮች የተንጸባረቁ ተግዳሮቶች ያልዋቸውን ዘርዝረዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የዶላር ዋጋ መጠንከር እድገትን እንደገደበ፣ የመዋዕለ-ነዋይ ፍሰት ዝቅ ማለትና የስራ-እጥነት መበራከት በአውሮፓ ቀጠና ያሉትን ሃገሮች አላንቀሳቅስ ማለቱን እንዲሁም የእድገት መዳከምና የገንዘብ ግሽበት ተጣምረው የጃፓን ኢኮኖሚን እየጎዱ መሆናቸውን የአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ሃላፊዋ አስገንዝበዋል።

ለጋርድ በሌላ በኩል ደግሞ ብሩህ ተስፋ የታየባቸው ያልዋቸውን ሃገሮች መጥቀሳቸው አልቀረም። በህንድ ጠንካራ እድገትና የገቢ ከፍ ማለት ታይቷል። በደቡብ ምስራቅ እስያ ኢንዶኒዥያ፣ ማሌዥያ፣ ዘፍሊፒኒስ፣ ታይላንድና ቭየትናም ጥሩ እየሰሩ ናቸው ብለዋል ለጋርድ።

XS
SM
MD
LG