በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ብር የውጭ ምንዛሪ አቅም ተቀነሰ


6ዶላር ከ06 ሳንቲም=100ብር
6ዶላር ከ06 ሳንቲም=100ብር

የኢትዮጵያን የምጣኔ ኃብት ዕድገት ለማሳደግ የተያዘው ጥረት አካል መሆኑ የተነገረለትን ዕርምጃ የምጣኔ ሃብት ባለ ሞያዎች በአዎንታ የተቀበሉት ቢሆንም የዋጋ ግሽበትን ያስከትላል የሚል ሥጋት አሳድሯል

ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገችው እርምጃ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ዶላር በኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ቀድሞ ከነበረው የ17 በመቶ ብልጫ ይኖረዋል።
የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት IMF የአዲስ አበባ ተጠሪ፥ Sukhwider Singh Toor ጨምሮ አንዳንድ የምጣኔ ሃብት ባለ ሞያዎች በአዎንታ የተቀበሉት ቢሆንም፤ ተገቢ በሆነ የገንዘብ ፖሊሲ እንዲደገፍ የሚሹ መሆናቸውን ይናገራሉ።
ኢትዮጵያው ላለፉት ሰባት ዓመታት በተከታታይ ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ዕድገት ማስመዝገቧን የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ ሲገልፅ ቆይቷል። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲና በተባበሩት መንግስታት በቅርቡ ይፋ የተደረገ የአገራትን የድህነት ይዞታ የሚያሳይ የጥናት ሠነድ በበኩሉ ኢትዮጵያን ከኒጀር ቀጥሎ የዓለም ሁለተኛዋ ደሃ አገር ማድረጉ ይታወሳል። የውጭ ምንዛሪ ቅናሹን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የተጠናቀረውን ዘገባ ዝርዝር ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG