በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ይዞታ የመንግስት እና የተቃዋሚዎች የተለያዩ ትንተናዎች


የኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ይዞታ ትንተናዎች አብዛኛውን ጊዜ ታማኝነት ያለው ገለልተኛ መረጃ ላይ ለማተኮር አይቻላቸውም። ምክንያቱም በመላ አገሪቱ የምርት፣ የእድገትና ለውጥ አሃዞችን የሚያጠናቅረው መንግስቱ በመሆኑ። በመረጃው ሙሉነት የሚነሱ ሙያዊ ወይንም ፖለቲካዊ ልዩነቶችን ታሳቢ አድርገን፤ የሚሰጡትን አሃዞች እንመልከት።

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው አመት የአገሪቱ ኢኮኖሚ በ11 ከመቶ ማደጉን ይናገራል። በቀጣዩም አመት ያስቀመጠው ትንበያ ከ11ከመቶ ያላነሰ እንድገት እንደሚኖር ነው። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ሰኞ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ይህንኑ አረጋግጠዋል።

“ባሳለፍንው ዓመት ከ11 በመቶ የማያንስ እድገት እንደምታስመዘግብ ይጠበቃል። በዚህ መሰረት አገራችን ለዘጠንኛ ጊዜ ባለ ሁለት አሃዝ በማስመዝገብ ፈጣን እድገት ለማስቀጠል ችላለች” ብለዋል ፕሬዝደንት ግርማ።

በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ የተቃዋሚው ፓርቲ መድረክ እሁድለት ባካሄደው የምጣኔ ሀብት ግምገማ ላይ ሰፊ ተንተና የሰጡት አቶ ተመስገን ዘውዴ፤ በቀደመው ፓርላማ የገዥው ፓርቲ የአጠቃላይ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲዎችን በመተቸት ይታወቃሉ። ይሄ እድገት የቁጥር እንጂ፤ ለህብረተሰቡ ጠብ ያለ ነገር የለም ባይ ናቸው።

“ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ውድቀት አየተከሰተ ነው፡፡ ሸማቹን ህብረተሰብ ያስጎነበሰ ሰቆቃ ላይ የጣለ፤ ዜጎች በገቢያቸው እንዳይተዳደሩ ያደረገ፣ ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት እንዳይልኩ ይደረገ ፣ የወር ገቢያቸውን ተቆጣጥረው እንዳይኖሩ ያደረገ ነው” ብለዋል አቶ ተመስገን።
ተመስገን ዘውዴ
ተመስገን ዘውዴ


ባለፈው ሳምንት አመታዊ የምጣኔ ሀብት ግምገማውን ይፋ ያደረገው የአለም የገንዘብ ድርጅት IMF የቀጣዩ አመት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ወደ 6.5 ከመቶ ዝቅ እንደሚል አስታውቋል።

አስቀድመው የተመዘገቡ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገቶን ከመቀዛቀዝ ለማዳን IMF የሰጠው ምክር በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት በተለይ በመሰረተ ልማት ግንባታው የግል-ዘርፉ ሚና እንዲጨምር ማድረግ የሚል ነው። እስካለፈው ሀምሌ ወር መጀመሪያ ድረስ የ7ከመቶ አጠቃላይ እድገት መመዝገቡን የጠቀሰው IMF የዋጋ ግሽበቱ በተመሳሳይ ጊዜ 33 ከመቶ መሆኑን አስታውቋል።

ጥያቄ የትኛው አሃዝ ነው ትክክለኛው? የንግድና ምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ላይ ዘገባ የሚያቀርበው የፎርቹን ጋዜጣ ስራአስኪያጅ-አዘጋጅ ታምራት ገብረጊዮርጊስ
“የIMF መግለጫ የወደፈቱን ማለትም በ2013 የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ 6.5 ከመቶ ሊያድግ ይቸላል ነው የሚለው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ደግም ወደ 11 በመቶ ይድጋል ብሎ ይተነብያል፡ በእድገትና ትራንስፎርሜሽኑ እቅዱ መሰረት፡፡ አንደኛው ከሌላኛው ትክክል ወይም ስህተት ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ሁለቱም በየራሳቸው መንገድ የወደፊቱን ነው የሚናገሩት፡፡ አመቱ ሲያልቅ የትኛው ትክክል እንደሆነ የምናየው የሆናል፡፡” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያው ፕሬዝደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በፓርላማ ያቀረቡት በተለይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲዎች የተገኙ እመርታዎች ላይ ያተኮረ መግለጫ፤ የዘርፍ እድገቶችን በደፈናው ገልጸዋል።

በኣገራችን ልማትን ለማፋጠን በተያዘው እቅድ መሰረት ግብርና መር ልማት ስትራቴጂው ተግባራዊነት ተጠናክሮ ሲቀጥል ቆይቶዋል፡ ምንም እንኳን ኢንዱስትሪ እና የአገልግሎት ዘርፍ አንዲሁም ግብርና ቢታሰብም በግብርናው መስክ ከፍተኛ የእድገት እድል እንዳለ በመገንዘብ ለዘርፉ ልማት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል ፡፡”

የአለም የኢኮኖሚ ፎረም (World Economic Forum) ባለፈው ሳምንት የአለም ተወዳዳሪነት ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያ በተቋማት ጥንካሬ፣ በመሰረተ ልማት፣ በአጠቃላይ ምጣኔ ሀብት፣ ጤናና ትምህርት ዙሪያ አገሮች ያሳዩት እድገት ተጨምቆ በሚቀርብበት ሰንጠረዥ ከአለም 144ኛ--ከአፍሪካ 38ኛ ሆናለች። በዚህ ደረጃ ያልተካተቱ የአፍሪካ አገሮች ስላሉ፤ የኢትዮጵያ ደረጃ በአፍሪካ የከፉ ከሚባለው የሚፈረጅ ነው።

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG