በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚደንት ሪያክ ማቻር በጥቂት ቀናት ውስጥ ዋና ከተማዋ ጁባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል


ይሁንና ምን ዓይነት አቀባበል እንደሚደረግላቸው እና መቼ ቃለ መሃላቸውን እንደሚፈጽሙ መንግስቱና ተቃዋሚዎቹ አሁንም ከስምምነት አልደረሱም።

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚደንት የሚሆኑት የአማጽያኑ መሪ ሪያክ ማቻር በጥቂት ቀናት ውስጥ ዋና ከተማዋ ጁባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይሁንና ምን ዓይነት አቀባበል እንደሚደረግላቸው እና መቼ ቃለ መሃላቸውን እንደሚፈጽሙ መንግስቱና ተቃዋሚዎቹ አሁንም ከስምምነት አልደረሱም።

የተቃዋሚው ኤስ ፒ ኤል ኤም (SPLM)ቃል አቀባይ ዊሊያም እዝኪዬል መሪያቸው የፊታችን ሰኞ ጁባ እንደሚገቡ ተስፋ አደርጋለሁ ብለው ነበር፣ ነገር ግን ሁለቱ ወገኖች ስለሚደረግላቸው አቀባበል አሁንም ዝግጅቱን አለማጠናቀቃቸውን ነው የገለጹት።

በኛ በኩል ያለን ስጋት እንደሚከተለው ነው። "የገቡ ዕለት ቃለ መሃላ ምፈጸም አለባቸው፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት አለበት። ጁባ ከጦር ሰራዊት ነጻ መሆንዋ በተኩስ አቁም እና የሽግግር ወቅት ጸጥታ ተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ አለበት።" ብለዋል።

ጁባ በሰላም ውሉ በተጠቀሰው መሰረት ከጦር ሰራዊት ነጸ መሆኑዋ ላይ ኣልረካንም ሲሉም ቃል ኣቀባዩ ኣመልክተዋል። የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር ማይክል ማኩኤ በበኩላቸው ጦሩን የማስወጣቱ ስራ ተጠናቅቁዋል ብለዋል።

የአማጽያኑ ቃል አቀባይ በበኩላቸው ማቻር ከመግባታቸው በፊት በተቆጣጣሪው አካል እንዲረገግጥልኝ እንፈልጋለን ያሉ ሲሆን የሰላም ውሉን ተግባራዊነት እንዲቆጣጣር የተሰየመው የጋራ ተቆጣጣሪ እና ገምጋሚ ኮሚሽኑን ባለልስልጣናት አስተያየት ለማግኘት አልተቻለም።

XS
SM
MD
LG