በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቃለ-ምልልስ ከየኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ከየኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ጋር


በማልታ የሚገኙ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት [ፎቶ ፋይል - ሮይተርስ]
በማልታ የሚገኙ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት [ፎቶ ፋይል - ሮይተርስ]

ውጭ ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ከሃገር ውስጥ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ሁከት አስመልክቶ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ።

በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ሁከት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የሃገሪቱ ባለሥልጣናት መግለጫ ሰጥተዋል።

የኮሚኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫና ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ሁከቱን ከበስተጀርባ ሆነው እያቀጣጠሉ ያሉት፥ በሀገር ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱና በውጭ ባሸባሪነት የተፈረጁ ቡድኖች ናቸው ሲሉ ከሰዋል።

በኮሚኒኬሽንስ ሚኒስትሩ ስለተሰጡ አስተያየቶች መልስ እንዲሰጡ፥ ለዛሬ በውጭ ያለውን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ከሃገር ውስጥ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስን ጋብዘናል።

ሰሎሞን ክፍሌ ነው ያነጋገራቸው ያጠናቀረውን ዘገባ ለማዳመት ከዚህ በታች ያለውን የድምች ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

ቃለ-ምልልስ ከየኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ከሃገር ውስጥ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:24 0:00

XS
SM
MD
LG