በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ሁኔታዎች ላይ አቋም እንዲወስድና ውሣኔ እንዲያሳልፍ ሃሣብ ቀርቧል


የአውሮፓ ፓርላማ አርማ (European Parliament logo) (አሶሽየትድ ፕረስ/AP)
የአውሮፓ ፓርላማ አርማ (European Parliament logo) (አሶሽየትድ ፕረስ/AP)

የአውሮፓ ፓርላማ ትናንት ባቀረበው የውሣኔ ሃሳብ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ የገመገመ፣ የተከናወኑ እንቅስቃሴዎችን ያጣቀሰና ግምት ውስጥ ያስገባ፣ የአውሮፓ ፓርላማ ኢንዲወስዳቸው እና የአውሮፓ ኮምሽንም ተፈፃሚ እንድያደርጋቸው የሚጠይቃቸውን እርምጃዎች ያካተተ ነው።

የአውሮፓ ፓርላማ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ሁኔታዎች ላይ አቋም እንዲወስድና ውሣኔ እንዲያሳልፍ የፓርላማው አባል የሆኑ ሶሻሊስቶች እና ዴሞክራቶች ጥምረት ቡድን ሃሣብ አቅርቧል፡፡

በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ቀድሞ የተወሰዱ እርምጃዎችን፣ ታኅሳስ 13/2008 ዓ.ም. የአውሮፓ የውጭ ጉዳይ የተግባር አገልግሎት ወይም በእንግሊዝኛ ምኅፃር ስሙ (EEAS - European External Action Service)፣ ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ያሉ ግጭቶችን እና የተከናወኑ እንቅስቃሴዎችን ያጣቀሰና ግምት ውስጥ ያስገባ ነው።

እንዲሁም የአውሮፓ ኮሚሽን የውጭ ጉዳዮችና የደህንነት ፖሊሲ፣ የአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ተጠሪና ምክትል ፕሬዚዳንት ፌዴሪካ ሞኼሪኒና የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም በጋራ የሰጡትን መግለጫና ባለፈው ሣምንት ጥር 14/ 2008 ዓ.ም. ባለስልጣናቱ ባደረጉት ስብሰባ ላይ የወጣው የፕሬስ መግለጫም ይጠቅሳል።በተጨማሪም፣ ኢትዮጵያ ግንቦት 16/2007 ዓ.ም. ባካሄደችው ምርጫ ላይ የአውሮፓ የውጭ ጉዳዮች የተግባር አገልግሎቱ ያወጣውን መግለጫ እና ሌሎች ክስተቶችን ያካተተ ነው። የጥምረት ቡድኑን ሃሣብ በእንግሊዝኛ ለማበብ ይህንን ፋይል ይጫኑ

ሰሎሞን አባተ ዝርዝሩን አጠናቅሮ አቅርቦታል፣ ከዚህ በታች ካለው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ሁኔታዎች ላይ አቋም እንዲወስድና ውሣኔ እንዲያሳልፍ ሃሣብ አቅርቧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:47 0:00

XS
SM
MD
LG