በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ተነጋገሩ


የአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ተጠሪና ምክትል ፕሬዚዳንት ፌዴሪካ ሞኼሪኒና

ሰሞኑን ኦሮምያና አማራ ክልሎች ውስጥ በታዩት ያለመረጋጋት ሁኔታዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በወሰዳቸው እርምጃዎች ላይ የአውሮፓ ኅብረት ምክትል ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተወያዩ፡፡

ሰሞኑን ኦሮምያና አማራ ክልሎች ውስጥ በታዩት ያለመረጋጋት ሁኔታዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በወሰዳቸው እርምጃዎች ላይ የአውሮፓ ኅብረት ምክትል ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተወያዩ።

የኅብረቱ ከፍተኛ ተጠሪና ምክትል ፕሬዚዳንት ፌዴሪካ ሞኼሪኒና የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ትናንት የኅብረቱ መቀመጫ በሆነችው የቤልጅየም ዋና ከተማ ብራስልስ ተገናኝተው የተመካከሩት ሁለቱ ወገኖች ግንኙነቶቻቸውን ለማጠናከር ባለፈው ጥቅምት ሞኼሪኒ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው በነበረበት ወቅት በተነጋገሩት መሠረት እንደሆነ ተገልጿል

በሌላ በኩል የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ አውሮፓ ኅብረት የተጓዙት ሰሞኑን ኦሮሚያ ውስጥ እየታየ ካለው የተቃውሞ እንቅስቃሴና መንግሥት የሰጠውን ምላሽ፤ እንዲሁም በሃገሪቱ የተከሰተውን የምግብ እጥረት ሁኔታ ለማስረዳት እንደሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ቡድን ሂዩማን ራይትስ ዋች ሰሞኑን አስታውቆ እንደነበር ይታወሣል።

የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾቹ ጥያቄአቸውን ለአውሮፓ ኅብረት አቅርበው እንደነበርም በቀደመ ዘገባ ተነግሯል።

ፋይል ፎቶ - የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም እአአ 2015
ፋይል ፎቶ - የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም እአአ 2015

የአውሮፓ ኅብረት ትናንት በበተነው የፕሬስ መግለጫ ሁለቱ ባለሥልጣናት ሲቪል ማኅበራትን በማጠናከር አስፈላጊነት፤ በሃሣብን በመግለፅና በመደራጀት ነፃነት ላይ መወያየታቸውን አመልክቷል።

በአውሮፓ ኅብረትና በኢትዮጵያ ስልታዊ ግንኙነቶች ላይ ያላቸውን ሥራ ለመቀጠል መስማማታቸውም ተገልጿል።

የኢትዮጵያን የልማት ማሻሻያዎችና ማኅበራዊና የምጣኔ ኃብት ዕድገቷን ለመደገፈ የአውሮፓ ኅብረት የመጀመሪያው አጋሯ መሆኗን የተናገሩት ሞኼሪኒ በዚህ ዓመት የሚካሄደውን የአውሮፓ ኅብረት - ኢትዮጵያ የንግድ መድረክ ወይም ቢዝነስ ፎረም ዝግጅት ጨምሮ ኅብረቱ ኢትዮጵያን በልማት ትብብር መርኃግብሮች ማገዙን እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ በሁለት ተከታታይ ድርቆችና ኤል-ኒኞ በፈጠረው ችግር ምክንያት የደረሰባትን ለመቋቋም ኅብረቱ የሚሰጠው እርዳታ ተጠቃሚ እንደምትሆንም ተነግሯል።

በፍልሰትና በእንቅስቃሴ ላይ የኢትዮጵያና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ አጀንዳ በሚል ባለፈው ኅዳር 1 በላቫሊታ ጉባዔ ወቅት የተፈረመውን ስምምነትም አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩና የኅብረቱ ምክትል ፕሬዚዳንት መወያየታቸው ታውቋል።

በዚያ ስምምነት ላይም ኢትዮጵያና የአውሮፓ ኅብረት መደበኛ ያልሆነውን ፍልሰት ችግር ለመጋፈጥ አብረው ለመሥራት መስማማታቸው ተነግሯል።

የአውሮፓ ኅብረት መሪ ሞኼሪኒ ኢትዮጵያ ሰባት መቶ ሺህ የሚሆኑ ስደተኞችን በማስጠለሏ አድናቆታቸውን የገለፁ ሲሆን የአፍሪካ አጣዳፊ ሁኔታ ፈንድም ኢትዮጵያ ውስጥ የተለየዩ ፕሮጀክቶችን መደገፍ መጀመሩ ተገልጿል።

በአፍሪካ ቀንድና በቀይ ባሕር አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይም ሁለቱ ባለሥልጣናት መነጋገራቸውን የኅብረቱ የፕሬስ መግለጫ አመልክቷል። ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ተነጋገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:46 0:00

አስተያየቶችን ይዩ (1)

XS
SM
MD
LG