በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአርበኞች ግንቦት 7 መሪዎች በዋሽንግተን ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ንግግር አደረጉ


ፋይል ፎቶ - የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ-መንበር ዶክተር ብርሀኑ ነጋ
ፋይል ፎቶ - የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ-መንበር ዶክተር ብርሀኑ ነጋ

አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ለትግል በረሀ የገቡበትን ምክናት አስረድተዋል። ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ደግሞ በኢትዮጵያ ስላለው የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሁኔታ፣ ስለ ድርቅና ረሀብ እንዲሁም ስለድርጅታቸው ትግል በሰፊው ተናግረዋል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ-መንበር ዶክተር ብርሀኑ ነጋና ጓዳቸው አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ትላንት እሁድ ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው ዳብል ትሪ ሆቴል ለኢትዮጵያውያን ንግግር አድርገዋል።

አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ለትግል በረሀ የገቡበትን ምክንያት አስረድተዋል። ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ደግሞ በኢትዮጵያ ስላለው የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሁኔታ፣ ስለ ድርቅና ረሀብ እንዲሁም ስለድርጅታቸው ትግል በሰፊው ተናግረዋል።

ንግግሩን ለመስማት በአደራሹ ከተገኙት ሰዎች ብዛት የተነሳ አደራሹ ከዳር እስከ ዳር ሞልቶ በኮሪደሩ ቆመው የሚሰሙትም ብዙ ነበሩ።

ባልደረባችን አዳነች ፍሰሀየ በቦታው ተገኝታ ያጠናቀረችው ዘገባ አለ ከዚህ በታች ካለው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የአርበኞች ግንቦት 7 መሪዎች በዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ንግግር አደረጉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:31 0:00

XS
SM
MD
LG