ዋሽንግተን ዲሲ —
በዚህ ፈታኝ ጉዞ ውስጥ ወጣቶች እንደወጡ ይቀራሉ፣ ከሞት የተረፉትም ለዘረፋ፣ለብዝበዛ ይጋለጣሉ፣ ሴቶችና ህፃናት ይደፈራሉ ለወሲብ ንግድም ይጋለጣሉ። ታዲያ የመንገዱን መከራ ሲያልፉ በገቡበት ሃገር ደግሞ ሌላ መከራ ይጠብቃቸዋል። ሕጋዊ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የላቸውም፤ ለማግኘትም መንገዱ በጣም ጠባብ ነው።
በእግርና በጀልባ ለወራቶች ተጉዘው ሳውድ አረቢያ ከገቡት ጥቂት ወጣቶች ውስጥ አንዱ ነው ሰኢድ። በኢትዮጵያ ሳለ ተማሪ ነበር። የራሱንና የቤተሰቡን ህይወት ለመለወጥ ፈለገና፤ ወደ ውጭ ተመለከተ፤ ወደ መካከለኛው ምስራቅ። የአረብ ሀገር ጉዞ ፈተናውን ጨረስኩ ሲል በሳውዲ አረቢያ ሰርቶ ለማደር የሚያስችል ፈቃድ ስለሌለው አሁን የየዕለት ፈተና ውስጥ ይገኛል። ስላለበት ሁኔታ ለመስታወት አራጋው እንዲህ አጫውቷታል።
ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያዳምጡ።