በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳዑዲው ወከባና ሊያስከትል የሚችላቸው የአእምሮ ጤና ጉዳቶች


የሳዑዲው ወከባና ሊያስከትል የሚችላቸው የአእምሮ ጤና ጉዳቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:20 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገር የተመለሱ ቁጥራቸው በብዙ ሺዎች የሚገመት ኢትዮጵያውያን የአካልና የስነልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸውና እንዲሁም ንብረታቸዉን ለማጣት መዳረጋቸውን ይናገራሉ። ሴቶች በግዳጅ እንደተደፈሩ እንደተደበደቡ፣ በእስር ቤት እንደተሰቃዩና ከመሃከላቸዉ ለሞት የተዳረጉትን እንኳን መቅበር ያለመቻላቸው ያደረሰባቸውን ተደራራቢ የመንፈስና የአካል ጉዳት ያስረዳሉ።

ከበረታው ስቃይና ፈተና ተርፈዉ አገር ከገቡ በኋላ በጉዳቱ የተነሳ የሚከሰት የአእምሮ ጤና መታወክ የሚገጥማቸው መኖራቸው ይታመናል። ወደ አገር ከተመለሱ በኋላ ሊደረግላቸዉ የሚገባ እንክብካቤና ድጋፍን አስመልክቶ የባለሞያ ምክር ጉዳዩን ይመረምራል።

አሜሊያ ሚሳይሊደስ በWahington DC የሚገኝ አንድ የማህበረሰብና ቤተሰብ አገልግሎት ማእከል ምክትል ዲሬክተር ናቸዉ። በDistrict of Colombia ዩኒቨርሲቲ በመምህርነትም ያገለግላሉ።

በሳዑዲው ወከባ ለጉዳት በተዳረጉ ኢትዮጵያውያን የአእምሮ ጤና ላይ ሁኔታው ሊያደርስ የሚችለውን የዳሰሰውን ውይይት ከዚህ ያድምጡ።

የሳዑዲው ወከባና ሊያስከትል የሚችላቸው የአእምሮ ጤና ጉዳቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:20 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG