በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሥራ ሦስት ሺህ ኢትዮጵያዊያን ተመልሰዋል፤ ሰልፎቹ እንደቀጠሉ ነው


በሮማው ሰልፍ ላይ ኤርትራዊያንና ሱዳናዊያንም አደባባይ ወጥተው ከኢትዮጵያዊያኑ ጎን ቆመዋል
በሮማው ሰልፍ ላይ ኤርትራዊያንና ሱዳናዊያንም አደባባይ ወጥተው ከኢትዮጵያዊያኑ ጎን ቆመዋል

ዋሽንግተን ዲ.ሲ ውስጥ ሰሞኑን ከተካሄዱት ሰልፎች አንዱ /ፎቶ - ኢትዮትዩብ/
ዋሽንግተን ዲ.ሲ ውስጥ ሰሞኑን ከተካሄዱት ሰልፎች አንዱ /ፎቶ - ኢትዮትዩብ/

please wait

No media source currently available

0:00 0:26:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ወደ አሥራ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን እስከአሁን ከሣዑዲ አረቢያ አዲስ አበባ መግባታቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የለንደኑ ሰልፍ
የለንደኑ ሰልፍ
ተመላሾቹን ለማቋቋም በፌደራል መንግሥቱና በክልል አስተዳደሮች የትብብር ሥራ እንደሚከናወንም መሥሪያ ቤቱ አመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ተፈፅሟል የሚል ዜና ከወጣ ጀምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን እያሰሙ ነው፡፡

ከአውሮፓ ሰልፎች ከአንዱ ላይ የተወሰደ
ከአውሮፓ ሰልፎች ከአንዱ ላይ የተወሰደ
ዛሬ፣ ሐሙስ፣ ኀዳር 12 / 2006 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጅና ጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ውስጥ ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡

ባለፉ ጥቂት ቀናት ውስጥም በእንግሊዝ፣ በጣልያን፣ በአውስትራሊያ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ደግሞ በዳላስ፣ በሎስ አንጀለስ እና በአትላንታ ከተሞች ተመሣሣይ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡

ከአውሮፓ ሰልፎች ከአንዱ ላይ የተወሰደ
ከአውሮፓ ሰልፎች ከአንዱ ላይ የተወሰደ

በአውሮፓና በአሜሪካ ከተደረጉት ሠልፎች የአንዳንዶቹን አስተባባሪዎች ቪኦኤ አነጋግሯል፡፡

ለዝርዝሩ ከአዲስ አበባና ከዋሽንግተን ዲ.ሲ የተቀናበሩ ዘገባዎችን ያካተተውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG