በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሣዑዲ ፍልሰተኛ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ሂዩማን ራይትስ ዋች እና ተመድ


ዩኤንኤችሲአር - ሂዩማን ራይትስ ዋች
ዩኤንኤችሲአር - ሂዩማን ራይትስ ዋች


በሳዑዲ አረቢያ የመመለሻ ሠፈር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያን
በሳዑዲ አረቢያ የመመለሻ ሠፈር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያን

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:12 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኛ ሠራተኞች ላይ እንደደረሱ በስደተኞቹ የሚገለፁ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎችን የሣዑዲ አረቢያ መንግሥት እንዲያጣራ የመብቶች ተሟጋች ቡድኑ ሂዩማን ራይትስ ዋች ጠየቀ።

ቡድኑ ኢትዮጵያዊያን ሠራተኞች በሳዑዲ ደረሱብን ያሏቸውን የመብቶች ረገጣዎች በዝርዝር አስቀምጦ፤ ጉዳዩ ተጣርቶ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር ከሳኡዲ አረቢያ እየተመለሱ ላሉ ኢትዮጵያዊያን የፍልሰት ሠራተኞች ሰብአዊ እርዳታ ማድረግ መጀመሩን ገልጿል።

እርዳታው ከኮሚሽኑ ግዴታ ውጭ ቢሆንም ሰብአዊ ቀውስ ሲከሰት በዝምታ ማለፍ እንደማይቻልም አመልክቷል።

ይህ እርምጃ በቅርቡ አንዲት የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣን ሰጡ ከተባለው አስተያየት ጋርም አይገናኝም ብሏል፡፡

የመለስካቸው አምሃና የሄኖክ ሰማእግዜር ዘገባዎች ዝርዝሩን ይዘዋል፤ ከላይ የተሰፈረውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG