ዋሸንግተን ዲሲ —
በሰንዳፋ ከ160 በላይ ሰዎች ተይዘው ወደ ሆለታ መሄዳቸውንና አንድ የ 15 ዓመት ልጅ በፀጥታ ሹሙ መገደሉን ነዋሪዎች ሲናገሩ፥ ባለሥልጣኑ ግን አስተባብለዋል።
በወለጋ ጊምቢ ከተማ የመንግሥቱ ኃይሎች ሕዝቡ እንዳይይንቀሳቀስ አግደዋል። ወጣቱ ከተማዋን ለቆ እንዲወጣ ጠይቀዋል ተብሏል።
በከተማዋ መደብሮች የሚዘጉ፥ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ያቋረጡ ፀረ-ሰላም ኃይሎች አሉ ሲሉ የጊምቢ ፖሊስ አዛዥ ተናግረዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።