ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ቀጥተኛ የውጭ መዋእለ ንዋይ ፍሰት እያደገ ቢመጣም በቂ አይደለም ይላሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጥናት ያከናወኑት ዶር አለማየሁ ገዳ።
ቀጥተኛ ያልሆነው ኢንቨስትመንት፤ ማለት በብድር የሚገኙና የመንግስት የመሰረተ-ልማትና ሌሎች ስራዎችን ለማከናወን የሚውል የገንዘብ ፍሰት በእጅጉ ከፍተኛ ነው።
በተለይ ከቻይና የተገኘው ብድር 17ቢሊዮን ዶላርስ በደረሰበት በአሁኑ ወቅት፤ ብድሩ እንዴት ይከፈላል? የወደፊቱን ትልውድና አሁን አጠቃላይ ምጣኔ ሀብቱ ላይ ምን አይነት ተጽኖ ይኖረዋል?
ሔኖክ ሰማእግዜር ከዶር አለማየሁ ጋር ያደረገውን ውይይት ያዳምጡ።