ዋሽንግተን ዲሲ —
ትላንት እሁድ በተጀመረው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ይፋ በማድረግ ለአፍሪካ ህብረት አባል ሃገሮች መሪዎች፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ለሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ይሰጣል። ዶ/ር አየለ በከሬ በመቐለ ዩኒቨርስቲ የታሪክና የባህል ጥናቶች ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው። ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው ኮርኔል ዩኒቨርስቲም ለብዙ አመታት የአፍሪካ ጥናቶች ክፍል አስተማሪ ነበሩ። ስለ እቅዱና አላማው ያብራሩልናል ያነጋገረቻቸው የአፍሪካ ነክ ርዕሶች አዘጋጅና አቅራቢ አዳነች ፍሰሃየ ናት። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ።