በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ህብረት በ27ኛ ጉባኤ አዲስ ሊቀመንበር እንደሚመርጥ ታወቀ


የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ድላሚና ዙማ
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ድላሚና ዙማ

የአፍሪካ ህብረት 27 ኛውን አመታዊ ጉባኤ በመጪው እሁድ ሩዋንዳ ይካሄዳል። በጉባኤው አብይ ቦታ የሚይዘው አዲስ ሊቀመንበር የመምረጥ ጉዳይ እንደሚሆን ታውቋል።

የአፍሪካ መሪዎች ኪጋሊ በሚሰበሰቡበት ወቅት ዋናው አጀንዳ ለአራት አመታት ያህል ድርጅቱን ሲመሩ የቆዩትን ኒኮሳዛና ድላሚና ዙማን የሚተካ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መምረጥ ይሆናል።

በአለም አቀፍ ደረጃ ስለሚከሰቱት ቀውሶች የሚከታተለው ኢንተርናሽናል ክራይስስ ቡድን የተባለው ድርጅት የአፍሪካ ህብረት አማካሪ ኤሊሳ ጆብሶን የአፍሪካ ህብረትን የሚመራው ማነው በሚለው ነጥብ ላይ ጫና ማደርጉ ወሳኝ ነው ይላሉ።

“የአፍሪካ ህብረትን የሚመራው ማነው በሚለው ነጥብ ላይ ጫና ማደርጉ ወሳኝ ይመስለኛል። የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና የጸጥታ አጀንዳዎችን መልክ የሚያስያዘው ሊቀመንበሩ ነውና። ስለሆነም ይህን ስልጣን የሚረከበው ለቦታው የሚገባ ሰው የመሆኑ ጉዳይ ወሳኝ ነው።”

ለቦታው ስማቸው ሲጠቅስ የቆዩት የቀድሞ የቦትስዋናና የቀድሞ የኢኳቶርያል ጊኒ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የቀድሞ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝደንት ናቸው። ኤችአይቪ/ኤድስን በሚመለከት በአፍሪካ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ልኡክ ነበሩ።

ዋሽንግተን በሚገኘው አትላንቲክ ካውንስ የአፍሪካ ማዕከል ስራ አስኪያጅ ጄ ፒተር ፋም ግን አዲስ ሊቀ-መንበር ለመምረጥ የሁለት ሶስተኛ ድምጽ እንዲኖር ስለሚያስፈልግ እሁድ በሚካሄደው ጉባኤ አዲስ ሊቀ-መንበር ላይመረጥ ይችላል ይላሉ።

በዛም ላይ አዲስ ምክትል ሊቀ-መንበርና ስምንት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነሮችም መመረጥ እንደዳለባቸው በዊልሰን ማዕከል የአፍሪካ ፕሮግራም ሃላፊ ሞንድ ሙያንጋዋ ገልጸዋል።

54 አባላትን ያቀፈው የአፍሪካ ህብረት ለአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ፓስፖርት የማውጣት እቅድም አለው። መጀመርያ ፓስፖርቶቹ ለህብረቱ አባል ሃገሮች መሪዎች፣ ለሀገራቱ ቋሚ ተወካዮችና ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ይሰጣሉ።

አለም አቀፍ የወንጀል ችሎትን በሚመለከት ደግሞ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገሮች ከችሎቱ አባልነት መውጣት ይኖርባቸው እንደሆነ ስትራቴጂ ለማውጣት አንድ የህብረቱ ኮሚቴ ባለፈው ጥር ወር ተመስርቶ ነበር።

ኮሚቴው ታድያ የአፍሪካ ሀገሮች ከችሎቱ አባልነት እንዳይወጡ ከተፈለገ አለም አቀፉ የወንጀል ችሎት በስልጣን ላይ ያሉ የሀገር መሪዎችና ከፍተኛ ባለስልጣኖች ሊከሰሱ የማይችሉበት ዋስትና መስጠት አለበት የሚል ሃሳብ አቅርቧል። በርካታ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ግን የችሎቱን ስኬታማነት ያዳክማል በሚል ይህን ሃሳብ አይቀበሉም።

ሁማን ራይትስ ዋች በተባለው የሰብአዊ መብት ተማጓች ቡድን የአለም አቀፍ ፍትህ ፕሮግራም ተባባሪ ስራ አስኪያጅ ኤሊስ ኬፕለር ኮሚቴው ያቀረበው ምክረ-ሃሳብ በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ይታይ እንደሆነ ግልጽ አይደልም ብለዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የአፍሪካ ህብረት በ27ኛ ጉባኤ አዲስ ሊቀመንበር እንደሚመርጥ ታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG