አዲስ አበባ —
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከሰኔ 27 ጀምሮ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የፈተናው ትናንት መቋረጥ አዲስ አበባ ውስጥ ላሉ ተፈታኞች አሣዛኝ መሆኑን ቪኦኤ ያነጋገራቸው አስረድተዋል።
ኦሮምያ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች የመዘጋጃ ጊዜ አላገኙም ያሉ የክልሉን የተቃውሞ እንቅስቃሴ የደገፉ ወገኖች የፈተናው መሠረቅና መቋረጥ ከዚሁ እንቅስቃሴ ጋር የተገናኘ መሆኑን እየገለፁ ናቸው።
መንግሥት በመረጃዎቹ ላይ መግለጫ አልሰጠም።
ለዚሁ ለተስተጓነለው ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና መቋረጥ በውጭ ሃገር የሚገኝ የኦሮሞ ተሟጋች ነኝ የሚል ቡድን ኃላፊነት ወስዷል።
በምኅፃር ኦኤምኤን (OMN) ተብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ሚድያ ኔትወርክ ዳይሬክተር ጃዋር መሃመድ ማምሻውን ለቪኦኤ በሰጠው መግለጫ ከስድስት ወራት በላይ ተቃውሞ ሲያካሂዱ የነበሩ የኦሮምያ ክልል ተማሪዎች የመማር ዕድል ስላልነበራቸው በተለይ የክልሉ ፈተና ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ መንግሥት ተጠይቆ ነበር ብሏል።
እስክንድር ፍሬው ተጨማሪ ዘገባ አለው፣ መስታወት አራጋውም ጃዋር መሃመድ ማምሻውን ትናንት ማምሻውን አነጋግራዋለች። ሁለቱንም ዘገባ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።