“የባርነት ተግባር እንደሚፈጸም ተረድተናል። ላልተወሰነ ጊዜ እስራት እንዳለ አውቀናል። ግድያ እንዳለ ተገንዝበናል። የማዋከብና የአስገድዶ መድፈር ተግባሮች እንደሚፈጸሙ፣ ሰዎች በወጡበት እንደሚቀሩ የማድረግ ወንጀሎች እንዳሉ ተረድተናል። እነዚህ ሁሉ ከባድ ወንጀሎች ናቸው”የመርማሪ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር ማይክ ስሚት
ማክሰኞለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኤርትራ ላይ የሰብዓዊ መብት ይዞታን እንዲመረምር የሰየመው መርማሪ ኮሚሽን የኤርትራ ባለስልጣናትና አስተዳድር በዜጎች ላይ ያደርሷቸዋል ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰጦች ዘርዝሮ፤ ተጠያቂነት እንዲኖር መክሯል።
“ያወጣነው ዘገባ ኤርትራ ውስጥ በስብእና ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ተደርገው የሚታዩ ዘርፈ ብዙ ወንጀልሎች መዝግቧል” ያሉት የመርማሪ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር ማይክ ስሚት ናቸው።
“የባርነት ተግባር እንደሚፈጸም ተረድተናል። ላልተወሰነ ጊዜ እስራት እንዳለ አውቀናል። ግድያ እንዳለ ተገንዝበናል። የማዋከብና የአስገድዶ መድፈር ተግባሮች እንደፈሚጸሙ፣ ሰዎች በወጡበት እንዲሚቀሩ የማድረግ ወንጀሎች እንዳሉ ተረድተናል። እነዚህ ሁሉ ከባድ ወንጀሎች ናቸው” ብለዋል።
የኤርትራን መንግስት አቋም ያብራሩት የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከፍተኛ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ የሰብዓዊ መብት መርማሪ ኮሚሽኑ ያወጣው ሪፖርት፤ አንድ ተጨማሪ የአፍሪካ ሀገርን ወደ አለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውሰድ የሚደረግ ጥረት አካል ነው ብለዋል።
ይሄን አጋጣሚ በመጠቀም በኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጀች ነው፤ ነገሩ የሁኔታዎች መገጣጠም ሳይሆን፤ አስቀድሞ የታሰበበት ነው ሲሉ አቶ የማነ ተናግረዋል።
“አሁን እየተነጋገርን ባለንበት ወቅት : ኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት ልታደርስ በመዘጋጀት ላይ ነች። ሙሉ ጦርነት ለመክፈትም በማሰብ ላይ ነች” ብለዋል አቶ የማነ።
የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ በኤርትራ በኩል የቀረበው ክስ መሰረት የሌለውና በዓለም አቀፍ የመብት ተቋማት የቀረበ አሳሳቢ ጥሰትን አቅጣጫ ለማስቀየር የታሰበ ነው ብሏል። የኮሚውኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለዝግጅት ክፍላችን እንዲህ ብለዋል።
“ዝግጅት እያደረግን አይደልም፤ ኤርትራ ለማጥቃት መዘጋጀትም አያስፈልገንም። ምክንያቱም ባለፈው ሳምንት የአስመራው አስተዳድር ላድረገብን ትንኮሳ የተመጠነ መልስ ሰጥተናል። ውጥረቱን ላለማባባስ በማሰብ ወታደሮቻችን ወደነበረው ቦታቸው ተመልሰዋል።”
“አሁን እየተነጋገርን ባለንበት ወቅት : ኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት ልታደርስ በመዘጋጀት ላይ ነች። ሙሉ ጦርነት ለመክፈትም በማሰብ ላይ ነች” ብለዋል አቶ የማነ።የኤርትራ ፕሬዝደንት አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት በኩል የሌሎች የአፍሪካ መሪዎች በአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ICC እንዳይከሰሱ ስትሰራ ከመቆየቷ ጋር ተያይዞ፤ በኤርትራ ላይ እንዴት የተለየ አቋም ተያዘ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ።
“የአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የአፍሪካ መሪዎች ላይ ማነጣጠሩን የአፍሪካ ህብረት በከፊል ሲቃወም ቆይቷል። ወንጀል ያለተጠያቂነት እንዲታለፍ ግን ደግፎ አያውቅም። መሪዎች ለሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ይፈልጋል።” ብለዋል።
የኤርትራ ፕሬዝደንት አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ በኤርትራ ላይ ውንጀላ የሚያቀርቡ አካላት በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ወደ ጎን የተው ናቸው ይላሉ።
“የአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የአፍሪካ መሪዎች ላይ ማነጣጠሩን የአፍሪካ ህብረት በከፊል ሲቃወም ቆይቷል። ወንጀል ያለተጠያቂነት እንዲታለፍ ግን ደግፎ አያውቅም። መሪዎች ለሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ይፈልጋል።የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ
“ኤርትራን ለመወንጀል የሚጉዋጉ ወገኖች በሰብዕና ላይ የሚፈጸም ወንጀል በራሱዋ ህዝብ ላይ የምትፈጽመው እና ጦርነት የምትከፍተው ኢትዮጵያ መሆንዋን ኣይተው እንዳላዩ ርምጃ ሳይወስዱ ኣንደሚቀሩ የሚታወቅ ነው።”
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።