በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ 18 ወታደሮች እንደሞቱባት አስታወቀች


ዩናይትድ ስቴይትስ ከኢትዮጵያ ጋር የሚከናወኑ የድንበር ግጭቶችን “ትቆሰቁሳለች” ስትል ኤርትራ ያወጣችው መግለጫ “እውነታ የለውም” ብላለች።

የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሰኔ 5 ቀን በጾረና ግንባር ከኢትዮጵያ ጋር በተካሄደው ከባድ ውጊያ በኤርትራ በኩል 18 ወታደሮች እንደሞቱ ገለጹ። ፕሬዝደንቱ ሰኞለት የኤርትራ ሰማእታት ቀን ሲከበር ባሰሙት ንግግር በኢትዮጵያ በኩል ተገደሉ ስለተባሉት ወታደሮች ቁጥር የተናገሩት ባይኖርም፤ ባለፈው ሳምንት የኤርትራ የማስታወቂያ ምንስቴር ባወጣው መግለጫ ከ200 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውንና ከ300 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ይፋ አድርጎ ነበር።

የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ
የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ

“እሁድ የሰማእታትን የአደራ ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው፤ የአስተማሪዎቻቸውን ፈለግ ለተከትሉ 18 ማስዋእትነት የከፈሉ ጀግኖቻን ኩራት ይሰማችሁ በክብርም ይታወሱ” ብለዋል ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ።

“እሁድ የሰማእታትን የአደራ ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው፤ የአስተማሪዎቻቸውን ፈለግ ለተከትሉ 18 መስዋእትነት የከፈሉ ጀግኖቻን ኩራት ይሰማችሁ በክብርም ይታወሱ”
ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ

የኤርትራ መንግስት የሰጠው አሃዝ በነጻ ምንጭ የተረጋገጠ አይደለም። የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት “እኛ እያነባን ስላልሆነ” ቁጥሩን መግለጽ አያስፈልገንም ሲሉ፤ ከኤርትራ በኩል የተገለጸው ተዓማኒነት እንደሌለው ማስረዳታቸው ይታወሳል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤርትራ አምባሳደር ግርማ አስመሮም በኤርትራ በኩል “ማስረጃ አለ” ሲሉ ገልጸዋል።

የኤርትራ መንግስት ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ባወጣው መግለጫ ዩናይትድ ስቴይትስ ከኢትዮጵያ ጋር ወግና የድንበር ግጭቶችን “ትቆሰቁሳለች” ስትል ያወጣችው መግለጫ “እውነታ የለውም” ሲል የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

ዝርዝር መረጃዎችና ማረጋገጫዎችን ሳያቀርብ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ምንስቴር ያወጣው መግለጫ ባለፈው እሁድ በሁለቱ ሀገሮች መካከል በተካሄደው ውጊያና በሌሎች የድንበር ጉዳዮች ዩናይትድ ስቴይትስ “በጦር መሳሪያ አቅርቦት የተጠናከረ ጥቃት እንዲደርስ አግዛለች” ብሏል።

“ዩናይትድ ስቴይትስ በሁለቱም ሀገሮች መዲናዎች ባሉን ወኪሎችም ሆነ በኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መልእክተኞቻችን ኢትዮጵያና ኤርትራ በትግስት ነገሮች እንዳይባባሱ እስንዲሰሩ ጥሪ አቅርባለች”
የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ

የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ
የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ

የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ “ዩናይትድ ስቴይትስ በሁለቱም ሀገሮች መዲናዎች ባሉን ወኪሎችም ሆነ በኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መልእክተኞቻችን ኢትዮጵያና ኤርትራ በትግስት ነገሮች እንዳይባባሱ እስንዲሰሩ ጥሪ አቅርባለች” ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ኤርትራ 18 ወታደሮች እንደሞቱባት አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG