በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ ከ200 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገድያለሁ ስትል፤ ኢትዮጵያ በበኩሏ ሸሽቶ የሄደ በጦር አውድማው የሆነውን ሊያውቅ አይችልም ብላለች


ፋይል- ኤርትራዊ ወታደር የካቲት 17,2001
ፋይል- ኤርትራዊ ወታደር የካቲት 17,2001

ባለፈው እሁድ ሰኔ 5 ቀን በጾረና ግንባር በኩል ኢትዮጵያና ኤርትራ ባካሄዱት ከባድ ውጊያ ከ200 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገድያለሁ ሌሎች ከ300 በላይ የሚሆኑን አቁስያለሁ ሲል የኤርትራ መንግስት አስታወቀ።

የኤርትራ መንግስት ሃሙስ እለት ባወጣው መግለጫ የሰጠው አሃዝ በነጻ ምንጭ የተረጋገጠ አይደለም።

የኤርትራ የማስታወቂያ ምንስቴር በመግለጫው የኢትዮጵያ ሰራዊትንደቁሰንበወታደሮቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰናል ብሏል። የኢትዮጵያ ጦር ጥቃቱን ከጀመረባቸው ስፍራዎች እንዲያፈገፍግ አድርገናል ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ሲናገሩእያፈገፈገ ያለ ሰራዊት፣ የተበታተነ ጦር፣ ሸሽቶ የሄደው የጦር አውድማ ላይ ያለውን ሁኔታ ሊረዳበት የሚችልበት መንገድ የለምብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የደረሰበትንም ሆነ ያደረሰውን ጉዳት ከመግለጽ ተቆጥቧል።

ኤርትራ ለተበበሩት መንግስታት ጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ኢትዮጵያ ልኦላዊነቴን ተጋፍታ ጥቃት ከፍታብኛለች ስትል በአስቸኳይ ጉባዔ ጉዳዩን እንዲመረምርና እንዲያወግዝ በሳምንቱ መጀመሪያ መጠይቋን አስታውቃለች።

የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው የኤርትራ መንግስት ለማጥቃት ያደረገውን ሙከራ ቀልብሰን፤ ሰራዊቱ ዓላማውን አሳክቶ ወደ ስፍራው ተመልሷል ማለታቸው ይታወሳል።

እሁድለት በሁለቱ ሀገሮች ጾረና ድንበር አካባቢ የተካሄደው ውጊያ በከባድ መሳሪያ የታገዘና መጠነ ሰፊ መሆኑም ተዘግቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG