በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያና ኤርትራ የፖለቲካ መፍትሄ ያብጁ ሲል፤ ኢትዮጵያ ተቀብላለች ኤርትራ “ማውገዝ” እንጂ “ታቀቡ” ተገቢ አይደለም ብላለች


ዶ/ር ተወዳ አለሙ(ግራ) አምባ. ግርማ አስመሮም(ቀኝ)
ዶ/ር ተወዳ አለሙ(ግራ) አምባ. ግርማ አስመሮም(ቀኝ)

ሰኔ 5 ቀን ኢትዮጵያና ኤርትራ በጾረና አካባቢ ያደረጉት ከባድ ውጊያ ዩናይትድ ስቴይትስና ሌሎች የዓለም አቀፍ መንግስታትና ተቋማትን አሳስቧል። የአፍሪካ ህብረት፣ የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ሌሎችም፤ የሁለቱ ሀገሮች መንግስታት ከግጭት እንዲታቀቡ በመጠይቅ ላይ ናቸው።

በዛሬውለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን በቤልጀም ብራስልስ አስቀድሞ በተያዘ ቀጠሮ አግኝተው አነጋግረዋል። ዋና ጸሃፊ ባንኪ ሙን በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር የተከሰተውን ከባድ ውጊያ አስመልክቶ ስጋት እንደገባቸው ገልጸዋል። ጉዳዩን በፖለቲካ ውይይት በሰላም ለመፍታት ጥረት እንዲደረግና፣ መቆጠብ እንዲኖር አሳስበዋል።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተከሰተውን ከባድ ውጊያ አስመልክቶ የሚሰጠው መግለጫ፤ አጥቂውንና ተጠቂውን የለየ አጠቃላይ ጥሪ ስለሆነ፤ ተቀባይነት የለውም ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤርትራ አምባሳደር ግርማ አስመሮም ማምሻውን ገለጹ።

“ሁለቱም ወገኖች እንዲታገሱ የሚል ተገቢ አይደለም። ምክንያቱም ወንጀለኛውና ወንጀል የተፈጸመበት እኩል አይደለም” ብለዋል።

“እኛ በላያችን ላይ ወረራ ነው የተፈጸመው። የዓለም ህግ ተጥሷል። ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግስት፣ የወያኔ መንግስት መኮነን ነው ያለበት” ብለዋል አምባሳደር ግርማ አስመሮም።

“ሁለቱም ወገኖች እንዲታገሱ የሚል ተገቢ አይደለም። ምክንያቱም ወንጀለኛውና ወንጀል የተፈጸመበት እኩል አይደለም”
ግርማ አስመሮም

በመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ተቀዳ አለሙ መንግስታቸው የፖለቲካ ውይይት ጥሪውን ይቀበላል ብለዋል።

“እነዚህ መግለጫዎች በሙሉ ተቀባይነት ያላቸው ናቸው። የኛ ፖሊሲ ይሄ ችግር በሰላማዊ መንገድ መፈታት አለበት፣ ቁጭ ብለን መነጋገር አለብን የሚል ነው ብለዋል አምባሳደር ተቀዳ አለሙ።

“እነዚህ መግለጫዎች በሙሉ ተቀባይነት ያላቸው ናቸው። የኛ ፖሊሲ ይሄ ችግር በሰላማዊ መንገድ መፈታት አለበት፣ ቁጭ ብለን መነጋገር አለብን የሚል ነው”
ዶ/ር ተቀዳ አለሙ

የኢትዮጵያና ኤርትራ ሃይሎች ሰኔ 5 ቀን በድንበራቸው ያካሄዱት ውጊያ ለሁለቱም ሀገሮች መንግስታት እርምጃዎቻቸውን መለስ ብለው እንዲገመግሙ የሚጋብዝ ነው ሲል የዓለም አቀፉ ቀውስ ክትትል ቡድን ICG ገልጿል።

አስመራ ከረዥም ጊዜ መገለል ለመውጣት ፡አዲስ አበባ ደግሞ በዓለም ደረጃ ያላትን ተቀባይነትና ሚና ለመጠበቅ የሚጥሩ ናቸው ያለው የICG ትንተና፤ በቅርቡ የተከሰተው ግጭት ለረጂም ጊዜ ሲጓተት የቆየውን የድንበር ውዝግባቸውን እንዲፈቱ በር የሚከፍት ነው ብሏል። ይሄ ካልሆነ ይላል የዓለም አቀፉ ጥናት ቡድን መግለጫ፤ ሁለቱም ሀገሮች ህዝቦቻቸውን የማይጠቅምና ወደማያባራ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG