በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኢትዮጵያ ልኦላዊነቴን ተጋፍታ ጥቃት ከፍታብኛለች” ኤርትራ


ፋይል- አምባሣደር ግርማ አስመሮም
ፋይል- አምባሣደር ግርማ አስመሮም

ኤርትራ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ኢትዮጵያ ልኦላዊነቴን ተጋፍታ ጥቃት ከፍታብኛለች ስትል በአስቸኳይ ጉባዔ ጉዳዩን እንዲመረምርና እንዲያወግዝ ጠየቀች።

እሁድ ዕለት በሁለቱ ሀገሮች ጾረና ድንበር አካባቢ የተካሄደው ውጊያ በከባድ መሳሪያ የታገዘና መጠነ ሰፊ መሆኑም ተዘግቧል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ አምባሳደር ግርማ አስመሮምን ማምሻውን አነጋግረናል።

"ኢትዮጵያ ጥቃቱን የከፈተችው፤ በሀገር ውስጥ የሚታዩ የፖለቲካ፣ የብሄርና የምጣኔ ሀብት አለመረጋጋቶችን አቅጣጫ ለማስቀየር ነው፤ ጥቃቱን ማን እንደከፈተ ግልጽ ነው" ይላል የኤርትራ መግለጫ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

“ኢትዮጵያ ልኦላዊነቴን ተጋፍታ ጥቃት ከፍታብኛለች” ኤርትራ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:27 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG