በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብጽ አየር መንገድ አውሮፕላን አስገድዶ ቆጵሮስ እንዲያርፍ ያደረገው ጠላፊ በቁጥጥር ስር ውሏል

የግብጽ አየር መንገድ አውሮፕላን አስገድዶ ቆጵሮስ እንዲያርፍ ያደረገው ጠላፊ በቁጥጥር ስር ውሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:38 0:00

የግብጽ አየር መንገድ አውሮፕላን አስገድዶ ቆጵሮስ እንዲያርፍ ያደረገው ጠላፊ በቁጥጥር ስር ውሏል

የቆጵሮስ መንግሥት ቃል አቀባይ ኒኮስ ክሪስቶዱሊደስ በትዊተር ባወጡት መግለጫ ዛሬ ማክሰኞ ላርናካ አውሮፕላን ጣቢያ ተገዶ ያረፈው አውሮፕላን መንግደኞችና የበረራ ሰራተኞች በደህና ሁኔታ ላይ ናቸው ብለዋል።

የግብጽ አየር መንገድ አውሮፕላን አስገድዶ ቆጵሮስ እንዲያርፍ ያደረገው ጠላፊ በቁጥጥር ስር መዋሉንና መንገደኞቹ ታግተው የቆይበት ሁኔታም ማብቃቱን የደሴቲቱ ሀገር ባለልሥጣናት ገለጡ።

የቆጵሮስ መንግሥት ቃል አቀባይ ኒኮስ ክሪስቶዱሊደስ በትዊተር ባወጡት መግለጫ ዛሬ ማክሰኞ ላርናካ አውሮፕላን ጣቢያ ተገዶ ያረፈው አውሮፕላን መንግደኞችና የበረራ ሰራተኞች በደህና ሁኔታ ላይ ናቸው ብለዋል።

ጠላፊው ሰኢፍ ኤል ሙስጣፋ የሚባል ሰውም መሆኑ የቆጵሮስ እና የግብጽ ባለሥልጣናት የገለጹ ሲሆን ከግብጽ እስክንድሪያ ወደካይሮ በመብረር ላይ የነበረውን አውሮፕላን ለመጥለፍ ያነሳሳው ምክንያት በግልጽ አልታወቀም። የቆጵሮስ ፕሬዚደንት ኒኮስ አናስታሲያዲስ ጠለፋው ከሽብርተኝነት ጋር የተገናኘ አይደለም።

ባንዳንድ የዜና ዘገባዎች መሰረት ጠላፊው ቆጵሮስ ስለምትኖር የቀድሞ ባለቤቱን አምጡ ሲል ነበር። በሌላ ዘገባ መሰረት ደግሞ ከአውሮፓ ህበረት ባለስልጣናት መነጋግር እፈልጋለሁ ብሏል። የፈንጂ ቀበቶ ታጥቄአለሁ ሲል ነበር ያሉም እሉ። የሆነ ሆኖ ባለሥልጣናት ከጠላፊው ጋር እየተደራደሩ ቆይተው ሃምሳ አምስቱ መንገደኞች በደህና ከአውሮፕላኑ ወርደው እንዲሄዱ ፈቅደዋል።

ድንገቱ ለዓመታት በፖሌቲካ ሁከትና በሽብር ስጋት የምትታመሰው ግብጽ ወሳኝ የቱሪዝም አንዱስትሪዋን ይብሱን ሳይጎዳባት አይቀርም።

XS
SM
MD
LG