በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግብጽ የተከሰከሰው አውሮፕላን በአይሲስ ምክንያት እንዳልሆነ ተገልጿል


ግብጽ ውስጥ የተከሰከስው የሩስያ አውሮፕላን
ግብጽ ውስጥ የተከሰከስው የሩስያ አውሮፕላን

ግብጽ ውስጥ የተከሰከስው የሩስያ አውሮፕላን በአይሲስ ምክንያት ነው በማለት የእስላማዊው መንግስት ነኝ ባዩ ነውጠኛው ቡድን የሰጠውን ቃል ፕሮፓጋንዳ ነው በማለት የግብጹ መሪ አብዱል ፋታ አልሲሲ ዛሬ ማክሰኞ አስተባበሉ።

ግብጽ ውስጥ የተከሰከስው የሩስያ አውሮፕላን በአይሲስ ምክንያት ነው በማለት የእስላማዊው መንግስት ነኝ ባዩ ነውጠኛው ቡድን የሰጠውን ቃል ፕሮፓጋንዳ ነው በማለት የግብጹ መሪ አብዱል ፋታ አልሲሲ ዛሬ ማክሰኞ ገልጸዋል። በተጨማሪም የግብጽን መልካም ገጽታና የተረጋጋ ሰላም ማጥለምያና ማደፍረሻ አንዱ አካል ነው ብለው ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት አውሮፕላኑ የቴክኒክ ችግር እንዳልነበረበት ዘግበን ነበር (ይህንን ፋይል በመጫን ዘገባውን ያገኛሉ) ። የበረራ ዳይሬክተር አቶ ስሚርኖቭ አይሮፕላኑ እየበረረ ሳይሆን፣ ወደ መሬት እየወደቀ ነው የታየው ነው ገልጸው ነበር።

የዛሬውን ዘገባ ሙሉ ዝርዝር ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

በግብጽ የተከሰከሰው አውሮፕላን በአይሲስ ምክንያት እንዳልሆነ ተገልጿል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:46 0:00

XS
SM
MD
LG