በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብጽ በሲናይ ለተከሰከሰው የሩስያ አውሮፕላን የሽብርተኛ ተግባር ማስረጃ እንዳልተገኘ አስታወቀች


የግብጽ የሲቪል አቪየሺን ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እስካሁን የሽብርተኝነትም ሆነ የሌላ ህገወጥ ተግባር ምልክት አልተገኘም ብልዋል።

ግብጽ እአአ ባለፈው ጥቅምት 31 ሲናይ ልሳነ ምድር ላይ ተከስክሶ 224 ተሳፋሪዎች ያለቁበት የሩስያ አውሮፕላን አደጋ መርማሪዎቼ የሽብርተኛ ተግባር ማስረጃ አላገኙበትም ስትል አስታወቀች።

የግብጽ የሲቪል አቪየሺን ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአደጋውን መነሾ ለማወቅ ምርመራው መቀጠሉን ገልጦ ሆኖም እስካሁን የሽብርተኝነትም ሆነ የሌላ ህገወጥ ተግባር ምልክት አልተገኘም ብልዋል።

ሩስያና ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ምዕራባውያን ሃገሮች አውሮፕላኑ የወደቀው የተጫነ ቦምብ ፈንድቶ ነው ማለታቸው ይታወሳል። እስላማዊ መንግስት ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን ለኣደጋው ሃላፊነቱን መወሰዱንና የፈነዳው ቦምብ ያለውንም ፎቶ አሳይቷዋል።

የሜትሮጄት አየር መንገዱ አውሮፕላን የወደቀው ከግብጹዋ የሻርማአልሼክ መዝናኛ ተነስቶ መብረር እንደጀመረ ሲሆን አደጋው የሀገሪቱን ቱሪዝም ጎድቱዋል። ሩስያ እና እንግሊዝ ወደ ግብጽ በረራ አቋርጠዋል።

እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ቢድን አውሮፕላኑን የጣልነው ሩስያ ሶሪያ ውስጥ ለምታካሂደው የአየር ጥቃት ዘመቻ ለመበቀል ነው ማለቱ ይታውሳል።

XS
SM
MD
LG