በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤል ኒኞ የምስራቅ አፍሪቃ ሃገሮች ላይ ስጋት ጋርጧል


ኤል ኒኞ የተባለዉ የዓየር ንብረት ክስተት በመጠናከሩ በምስራቅና ደቡባዊ አፍሪቃ አስራ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት የረሃብ፣ የበሽታና የዉሃ እጥረት ቀዉስ እንደሚያሰጋቸዉ የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጂያ ድርጅት (UNICEF)ገለጸ። ኬንያና ኡጋንዳ ከባድ ጎርፍ ለመከላከል እየተዘጋጁ ሲሆን ደቡብ አፍሪቃና ማላዊ ደግሞ በድርቅ እየተሰቃዩ ነዉ ብልዋል።

ዋንስመስ ሩሬ(Onesmus Ruirie) የኬንያ የሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት ዋና ሃላፊ እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር ከ 1950 ዓ.ም. ሳይንቲስቶች ስለ ኤልኒኖ መዘገብ ከጀመሩ ወዲይ ከባዱ ሰለነበረዉ የ1997 እና 98 ቀዉስ ያስታዉሳሉ።

"በመላ ሃገሪቱ ዝናቡ በማየሉ ጎርፉ ሰው ፈጄ፣ በሽታ ተቀሰቀሰ መሰረተ ልማትም ወደመ። ስለዚህ የ97ቱ ኤል ኒኖ በጣም ከባድ ነበር።"

በኤል ኒኞ (El Nino)ምክንያት የተከሰተውን የፓሲፊክ ውቅያኖስን ሙቀት ለውጥ ናሳ ሳተላይቶች (NASA satellites) ከእአአ 1997 እስከ እአአ 2015

ዘንድሮ እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር በ2015ም የኤልኒኖ ክስተት አፍሪቃ ላይ ከባድ ቀዉስ ያደርሳል ይላሉ።

ኤል ኒኞ (El Nino) በምድር ሰቅ ላይ የሚገኘዉና ማእከላዊዉ የፓሲፊክ ዉቂያኖስ ሙቀት መጨመር ነዉ። ይህ የሚሆነዉም በየሁለት ዓመት በየሰባት ዓመት ጊዚያትእንደሆ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘዉ የዩናይትድ ስቴትስ (United States) ብሔራዊ የዉቂያኖስና የከባቢ ዓዬር ጉዳዮች መስሪያ ቤት የዓዬር ጠባይ ተንባይ ሜትሮሎጂስት ቶም ዲ ሊበርቶ (Tom Di Liberto) እንደሚሉት በዓለም የዓዬር ንብርት ላይ ከባድ እንድምታ ሊኖረዉ ይችላል።

"ይህንን አጉል የሆነ የውቅያኖስ ውሃ ሙቀት መጨመር ስንመለከት፤ በተለይ በምድረ ወገብ ዙሪያ የከባቢ አየርን ክፉኛ ለቅጧል። ውጤቱ ህልቁ መሳፍርት የለውም፤ አያባራም። ከሰላማዊ ውቅያኖስ ዳርቻዎች አልፎም የሌሎች አካባቢዎችን አየር ጠባይ ክፉኛ እየለወጠ ነው" ብለዋል።

ኤል ኒኞ በሚከስተበት ጊዜ በምስራቅ አፍሪቃ አገሮች ከባድ ዝናብ እንደሚጥል ሲጠበቅ በደቡባዊ አፍሪቃ በአዉስትራሊያና በኢንዶኔዜያ አካባቢ ደግሞ አብዛኛዉን ጊዜ ከባድ ይከሰታል የደን እሳት አደጋም ይበዛል።

ዋንስመስ ሩሬ(Onesmus Ruirie)በኢል ኒኖ ወቅት በተለይ መብስራቅ አፍሪካ የአየር ሁኔታው ፈጥኖ የሚለወጠው፤ ውሃው ሞቃታማ የሆነው የህንድ ውቅያኖስ ስለሚከበው ነው። ውሃ ሲሞቅ ይተናል። እርጥበት ያዘለው ውሃ ደግሞ በንፋስ ተገፍቶ ወደ የብስ በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ሲጠጋ ዝናብ ይሆናል። በስተደቡብ ግን ጠብ የሚል ዝናብ የለም። ለዚህ ነው ደቡባዊ አፍሪካ ላይ ድርቅ የሚታየው" ብለው አብራርተዋል።

ሆኖም ትንበያዉ ሁል ጊዜም እንደተጠበቀዉ አይከሰትም። እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር በ1997 ዓም ለምሳሌ በደቡባዊ አፍርቃ አገሮች ድርቅ እንደሚከሰት ተጠብቆ ቢሆንም አልሆነም። ኤል ኒኖ አካባቢን ማዉደም ብቻ ሳይሆን ጥቅምም እንዳለዉ ኬንያዊዉ ሜትሮሎጂስት ሩሬ(Ruirie) ተናግረዋል።

“በሰሜን ኬንያ ያሉ አካባቢዎች ድርቅ ይታይባቸዋል። ሲዘንብ ደግሞ ያወርደዋል። ስለዚህ የአካባቢው ነዋሪዎች ውሃ ለማቆር ኩሪዎችን እይቆፈሩ ነው። ስለዚህ የግጦሽ መስኮች እንደሚለመልሙ ነው የምንጠብቀው” ብለዋል።

የአሜሪካ (United States) ብሔራዊ የዉቂያኖስና የከባቢ ዓዬር ጉዳዮች መስሪያ ቤት የዓዬር ጠባይ ተንባይ ሜትሮሎጂስት ቶም ዲ ሊበርቶ (Tom Di Liberto ) የያዝነዉ ዓመት ሶስተኛዉን የኤል ኒኞ (El Nino) ጫና የምናስተዉልበት ሊሆን የችላል ግን ይህ የሚረጋገጠዉ መረጃዎች ሁሉ ተሰብስበዉ ሲጠናቀቁ በ አዉሮፓ 2016 መግቢያ ላይ ይሆናል ብለዋል።

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የምስራቅ አፍሪቃ ዘጋቢ ጅል ክሬግ (Jill Craige) ይህ ፓሲፊክ ዉቂያኖስ ላይ የተከሰተዉ ኤል ኒኞ የአየር ንብረት በአፍሪቃ ላይ የሚኖረዉን እንድምታ ዘግባለች። ትዝታ በላቸዉ አቀርበዋለች። የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ኤል ኒኞ የምስራቅ አፍሪቃ ሃገሮች ላይ ስጋት ጋርጧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:28 0:00

XS
SM
MD
LG