በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ድህነትን ለመቀነስ ባልተደራጁና ባልተረጋጉ ገበያዎች ንግድና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት

ድህነትን ለመቀነስ ባልተደራጁና ባልተረጋጉ ገበያዎች ንግድና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት


ወ/ሮ ሁጉተ ሳሙ ባኬኮሎ በስደት ለአስርት አመታት ስትኖር፤ ህልሟ የሀገሯ ኮንጎ የስልክ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት መመስረት ነበር
ወ/ሮ ሁጉተ ሳሙ ባኬኮሎ በስደት ለአስርት አመታት ስትኖር፤ ህልሟ የሀገሯ ኮንጎ የስልክ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት መመስረት ነበር

መንግስታዊና የግል ዘርፍ ባለሙያዎች ይሄን ችግር እንዴት በጋራ ሊያሻሽሉት እንደሚችሉ ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጉባዔ ውይይት ተደርጎበታል።

በዓለም የገበያ ስርዓት በአግባቡ የተደራጀ የምጣኔ ስርዓት እንዲሁም ሰላምና መረጋጋት ወሳኝ ናቸው። በተለይ የዓለማችን 2.5 ቢሊዮን ህዝብ በሚኖርባቸው ድሃ ሀገሮች የገበያ ስርዓትና የፖለቲካ አለመረጋጋት ነጋዴዎችና ባለሀብቶችን ያሼሻሉ።

መንግስታዊና የግል ዘርፍ ባለሙያዎች ይሄን ችግር እንዴት በጋራ ሊያሻሽሉት እንደሚችሉ ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጉባዔ ውይይት ተደርጎበታል።

በዓለማችን በመንግስት ብቻ ለምቶ ያደገ ሀገር የለም። መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችም እንዲሁ። በሁለቱም ዘርፎች ፍላጎቱ ቢኖርም፤ አቅሙ እንደሌለ ነው የመንግስት ወኪሎም የዓለም አቀፍ የገንዘብና ምጣኔ ባለሙያዎችም ያሰመሩበት። የግሉ ዘርፍ የምጣኔ ሀብት ተሳትፎ ለልማት፣ ፈጣን እድገትና ስራን በመፍጠር ረገድ እጅግ ከፍተኛ ነው።

የግል ሀብትና ንብረትን መሳብ እጅግ ከባድ ነው። ነጋዴ ዋናው አላማው ሰርቶ ማትረፍ ስለሆነ፤ ትልቁም የንግድ ተቋም ሆነ አነስተኛ ነጋዴዎች ገንዘባቸውን በአንድ ምጣኔ የሚያፈሱት ተጠንቅቀው፣ ገበያ አጥንተው፣ አዋጭነቱን ተረድተው ነው።

እነዚህን ሁሉ መሰረታዊ የንግድ አሰራሮች ለማከናወን ታዲያ መረጃ ያስፈልጋል። በተለይ የውጭ ኩባንያዎች በማያውቁት ሀገር፣ አዲስ በሆነ መዋቅር ሲሰሩ፤ ትርፋቸውንና ኪሳራቸውን ብቻ ሳይሆን፤ የማትረፍና የመክሰር እድላቸውን የሚገመግሙበት የመረጃ ቋት ይፈልጋሉ። ከዚያም አልፎ የገበያ ስርዓቱ በአግባቡ የተደራጄ እንዲሆን ይፈልጋሉ።

ጄኒፈር ኩክ የዓለም አቀፍ ስልት ጥናት ማእከል (CSIS) የአፍሪካ ክፍል ሃላፊ ናቸው። የግሉ ዘርፍ በአፍሪካ ምጣኔ ሀብት እንዲሳተፍ የየሀገሩ መንግስታት፣ ዓለም አቀፍ ተቋሞችና አጠቃላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት፤ የግንዛቤ ማስጨበጥና፤ መረጃን የማሰባሰብና በግልጽ የማሰራጨት ስራ ከፍተኛ ስፍራ ይሰጡታል።

"ዓለም አቀፉ የንግድ ማህበረሰብ አፍሪካን በአዲስ መልኩ እንዲመለከት፣ አህጉሪቷ የተለያዩ ሃገሮችና ባህሎች የሚንጸባረቁባት መሆኑን እንዲረዱ ማድረግ ነው። የትርፍ እድሎች ባሉበት ስፍራ ሁሉ ፈተና አለ። ስለዚህ የግሉ ዘርፍ በማያውቀው የገበያ ሁኔታ እንዲሰራ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ አስተማማኝ መረጃ ማቅረብና አሰራሮችን ማሻሻል ያስፈልጋል።" ብለዋል።

"ባለፈው ሳምንት በዓለም ባንክና የዓለም የገዘብ ድርጅት IMF ዓመታዊ ጉባዔዎች ውይይት ከተካሄደባቸው አንዱ ጉዳይ አስቸጋሪ በሆኑ ገበያዎችና ሀገሮች ስራ ለመፍጠር፣ ገቢን ለማሻሻልና የብድር አገልግሎቶችን ለማስፋፋት የግሉ ዘርፍ ምን አይነት ሚና ሊጫወት ይችላል፤ የመንግስትስ ሃላፊነት ምንድን ነው? በሚል ውይይት ተካሂዶበታል።" ይላሉ ጀኒፈር ኩክ።

"በጣም ወሳኝና ብዙ ፈተናዎች ያሉበት ነው። በቅድሚያ የመሰረተ ልማት ክፍተት አለ። የንግድ ስራን የሚያመቻቹ ተቋሞች ደካማ ናቸው፤ ቁጥጥር ለማድረግ ያለው ብቃትም እንዲሁ። መንግስታት በነዚህ የልማት ዘርፎች ተገቢ የሆኑ መዋቅራዊ ለውጦችን ለማድረግ ፍላጎታቸው አነስተኛ ሆኖ እናገኛለን።" በማለት አክለዋል።

የCSIS የአፍሪካ ክፍል መሪ ጄኒፈር ኩክ፤ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የአፍሪካ ሀገሮች ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ሊወስዱ የሚገቧቸው እርምጃዎችና ከሌሎች አጋሮች የሚያስፈልጓቸውን እግዛዎች ሲያብራሩ

"የተወሳሰቡ የኢንቨስትመንት ስምምነቶችን ለማስተዳድር የሚያስችላቸው አቅም መገንባት ያሻል። የተቋማት ግንባታ እዚህ ላይ ወሳኝ እርምጅ ይሆናል። ሌላኛው በአፍሪካ ያሉ መካከለኛና አነስተና የንግድ ተቋማት እንዲንቀሳቀሱ ማበረታታትና፤ እድገታቸውን ማመቻቸት ነው።" ብለዋል።

ሁጉተ ሳሙ ባኬኮሎ በስደት ለአስርት አመታት ስትኖር፤ ህልሟ የሀገሯ ኮንጎ የስልክ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት መመስረት ነበር። የተለያዩ ኩባንያዎች ለሽያሽና ደንበኛ አገልግሎት በስልክ የሚሰጧቸው ምላሾች የሚበዙት ከህንድና ሌሎች የኢስያ ሀገሮች ነው። ሀግዊና ባልደረባዋ አኒ፤ ይሄንን አገልግሎት ለምን በጎንጎ መሰረቱን አድርገን አናስፋፋውም ሲሉ ስራ ጀመሩ።

"አኒ እና እኔ በውጭ ሀገር በትምህርትና ስራ ላይ ሳለን፤ ለምን ወደ ኮንጎ ሄደን ስራ አንጀምርም አልን። በወቅቱ አኒ በቴሌኮሚውኒኬሽንስ ትሰራ ነበር። እኔ ደግሞ በስልክ የደምበኛ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ውስጥ እየሰራሁ ነበር። በኮንጎ ደምበኞችን በስልክ የማስተናገድ አገልግሎትን በማስተዳደር ረገድ ክፍተት እንደነበር በማወቃችን፤ ቀጠልንበት።" ብላለች።

ስራውን ለመጀመር የሚያስፈልጉ በርካታ የአስተዳድር፣ የገንዘብና ቴክኖሎጂ ውጣ ውረዶች ካለፉ በኋላ፤ በአፍሪካ ዙሪያ አዳዲስ መካከለኛና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች ከሚገጥሟቸው ፈተናዎች አንዱና ወሳኙ ብድር አለማግኘት ነበር። የብድር አገልግሎቱ ሲገኝም፤ ብዙ ቅድመ-ሁኔታዎችና ውጣ ውረዶች ነበሩበት።

"ባንኩ የጠየቅንውን ገንዘብ አልሰጠንም ነበር። ብድሩን የመክፈያ የችሮታ ጊዜም አልነበረውም። ግን ገንዘቡ ያስፈልገን ስለነበር ተበደርን። ከዚያ የዓለም አቀፍ እገዛ ከIFC አገኘንና ስራውን አስፋፍተን ቀጠልን።" በማለትም ሃሳቧን ገልጻለች።

እንደ ሁጉተና አኒ ያሉ አዳዲስ የንግድ ድርጅቶች በአፍሪካ ዙሪያ ስራ ለመፍጠርና ትርፋማ ለመሆን በሀሳቡና በንግድ እቅዱ ተማምነው ገንዘብ የሚያበድሩ ተቋማትና ግለሰቦች መዋእለንዋይ ሲያፈሱባቸው ነው። አፍሪካ በየዓመቱ ከ10 ሚሊዮን በላይ ስራዎችን ለሚመጡት አስርት ዓመታት መፍጠር ይጠበቅባታል። ለዚህ ግብ መሳካት የግሉ ዘርፍ ግንባር ቀደም ነው።

ድህነትን ለመቀነስ ባልተደራጁና ባልተረጋጉ ገበያዎች ንግድና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG