በመቶዎች የሚቆጠሩ የካሜሩን ወጣቶች ዛሬ በዋና ከተማ ያዉንዴ የሚገኝ ፓሊስ ጣቢያ አጥቅተዉ ቢያንስ አንድ ሰዉ ሲሞት አያሌ ሌሎች ቆስለዋል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ከያዉንዴ ገበያዎች ትልቁ የሚገኝበት የሞኮሎ (Mokolo) ፖሊስ ጣቢያን ሲያጠቁ ነዉ የሚሰማው። አንዳንዶቹ አገር ዉስጥ የተሰራ ጠመንጃ፣ ገጀራና ድንጋይ ይዘዋል።
በንግድ ስራ የሚተዳደሩ ድዜከም ማርያ (Dzzekem Maria) የተባሉ ሴት በተቃውሞው ከተሳተፉት መካከል ናቸው። እኛ ፖሊሶች የሚፈጽሙትን የጭካኔና የማስፈራራት ተግባርን ነው የምናቃወመው ብለዋል።
"ፖሊሶች እዚህ መጥተው ሰዎችን ያዋክባሉ፣ ይደበድባሉ። ሰዎችን ስለሚገድሉና በሚፈጽምዋቸው ተግብሮች ምክንያት በፖሊሶቹ ላይ ቁጣ አለብን። ባለፈው ጊዜ እዚህ መጥተው አንድን ሰው ገደሉ"ብለዋል።
በአከባቢው ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው የፖሊስ ሃላፊ ፎርሱዋ ማርቲን ችላውዴ (Forsua Martin Claude) ወጣቶቹ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የተገደለ ወጣትን እየተበቀሉ ነው ብለዋል።
ተጠርጣሪው ሰው የሞተው ገበያ ላይ ከአንዲት ሴት ገንዘብ ነጥቆ ፖሊስ ሊያስረው ሲል እምቢ በማለቱ ነው ይላሉ።
ፖሊስች ጥቃቱ ወደ ሌሎቹ ገበያዎችም ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው (Claude) ገልጸዋል።
ትቃቱ ከዋናው የፖሊስ ጣብያ በአከባቢው ወዳሉት የፖሊስ ቦታዎች መስፋፋት ቀጥለዋል። በገባያዎች ተጨማሪ ፖሊሶች እንዲመደቡ መጠየቃቸውን የፖሊስ ባለስልጣኑ ገልጸዋል።
በአከባቢው ያሉ ከፍተኝ የመንግስት ባለስልጣን የምፔን ኦስማን ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ ምክንያት በአከባቢው ሰላም እየተመለሰ ነው።የንግድ ስራዎችም በቅርቡ ስራቸውን መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ስለሙስና ጉዳይ የሚከታተለው አለም አቀፍ ተቋም ካሜሩን ከሰሀራ በመለስ ካሉት የከፋ ሙስኖ አለባቸው ከሚባሉት የአፍሪቃ ሀገሮች አንዷ ናት። ፖሊሶቹም እጅግ ሙሰኞች ከሚባሉት መካከል ናቸው ብሏል።
ዘጋቢአችን ሞኪ ኤድዊን ኪንድዘካ (Moki Edwin Kindzeka) ከያዉንዴ የላከዉ ሪፓርት አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች።