በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሊባን ዓለም አቀፋዊ እውቅና እየጠየቀ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የታሊባን ተዋጊዎች
ፎቶ ፋይል፦ የታሊባን ተዋጊዎች

ታሊባን የአፍጋኒስታን ህጋዊ ወኪል ስለ መሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ለማግኘት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ታሊባን በመግለጫው “የዲፕሎማሲው ጥረት የዓለም ደህንነትን በማረጋገጥና ለአስርት ዓመታት ያለማቋረጥ ጦርነት ውስጥ ሲሰቃይ የኖረውን የአፍጋኒስታን ህዝብ ስቃይ ለማቃለል ይረዳል” ብሏል፡፡

የእስልምና ቡድኑ የባህል ኮሚሽን ከፍተኛ አመራር አብዱል ጣኻር ባልኪ፣ ለቪኦኤ እንደተናገሩት “ሁሉን አካታች የሆነ እስላማዊ መንግሥት ለመመስረት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እየተካሄደ መሆኑን” ገልጸው “ ይህ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል” ብለዋል፡፡

አብዱል ጣሪህ ባልኪ “ ዓለም እኛን ብቻ ሳይሆን መላውን የሰው ልጅ የገጠሙትን ፣ ከደህንነት እስከ አየር ንብረት ለውጥ ድረስ ያሉትን ችግሮች በጋራና በአንድነት ለመቋቋም፣ አንድ ላይ መሆን የሚችልበት ልዩ አጋጣሚ የተፈጠረለት ይመስለኛል” ብለዋል፡፡

ባልኪ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ህጋዊ የአፍጋኒስታን ህጋዊ ወኪል ስለመሆናችን እውቅና እንደምናገኝ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ተችዎች ግን ታሊባን በቅርቡ ስለገባው ቃል አሁንም ጥርጣሬ ያላቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ቡድኑ ከአልቃይዳና ከሌሎች የአሸባሪ ድርጅቶች ጋር አሁንም ግንኙነት ያለው መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣናትም በቅርቡ ያወጡት ሪፖርት ግድያዎችና ታሊባን በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች በሴቶች ላይ የተጣሉ ገደቦች መኖራቸውን አመልክተዋል፡፡

ዩናትድ ስቴትስ እኤአ በየካቲት 2020 ከታሊባን ጋራ ባደረገችው ስምምነት ወታደሮችዋና በአፍጋኒስታኑ የ20 ዓመት ጦርነት አብረዋት የነበሩት ምዕራባውያን አጋሮችዋን እንዲወጡ መስማማቷ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ዋሽንግተንም ሆነ የተቀረው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ካቡል ላይ በኃይል ለሚመሰረት መንግሥት የሚሰጡት እውቅና እንደማይሰጡ ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG