በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜጎችን ከአፍጋኒስታን የማውጣቱ ሩጫ ቀጥሏል


ዜጎችን ከአፍጋኒስታን የማውጣቱ ሩጫ ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:42 0:00

ዜጎችን ከአፍጋኒስታን የማውጣቱ ሩጫ ቀጥሏል

ከአፍጋኒስታን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያንና የአፍጋን ዜጎችን ለማስወጣት የሚደረገው ሩጫ ቀጥሏል፡፡ ከነሀሴ 25 በኋላ ወደ የሚቀሩትን የአፍጋን ረዳቶች ለማውጣት ያለው እድል በግልጽ ባለመታወቁ በፍጥነት የማስወጣቱ እንቅስቃሴ ተጠናክሯል፡፡

በአፍጋኒስታን የሚገኙ አሜሪካውያንና ረዳት የአፍጋን ዜጎች ለማወጣት በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ካቡል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል፡፡

የአሜሪካ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ማርክ ሚሊ እንዲህ ይላሉ

“ይህ የኛ የግል ጉዳይ ነው፡፡ እናወጣቸዋለን፡፡ እስካሁን 5ሺ ያህል ሰዎችን ያወጣን ሲሆን ቁጥሩን ለመጨመርም እያሰብን ነው፡፡”

ይሁን እንጂ ከአውሮፕላን ማረፊያው ውጭ ያለው ሰዎችን ከአገር የማስወጣት እንቅስቃሴ ሁሉ፣ በታሊባኖች ቁጥጥርና ትብብር ስር መሆናቸው እየታወቀ ነው፡፡ ዩናይትድ ስቴትም ልታድናቸው ቃል የገባችውን የአሜሪካውያንና አፍጋን ረዳቶችን መተላለፊያ፣ ታሊባኖቹ እያገዱት ነው የሚል ዘገባም እየተሰማ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን ለሪፖርተሮች በሰጡት መግለጫ የአሜሪካ ወታደሮች ሙሉ ትኩረታቸውን የሚያደርጉት የአውሮፕላን ማረፊያውን ስፍራ በመከላከል ብቻ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ባላፈው ሰኞ በአውሮፕላን ጣቢያው በተፈጠረ ግርግርና መረበሽ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ትራፊክ ለሰዓታት ተገቶ የነበረ ሲሆን ለተወሰኑ ሰዎችም ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡

መከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስተን እንዲህ ብለዋል

“ አሁን ዝምብዬ ተነስቼ በመሄድ ካቡል ውስጥ ያለውን ኦፕሬሽን ለማስፋፋት የሚያስችል አቅም የለኝም፡፡”

ባለፈው እሁድ ካቡል የተፍረከረችው የቀድሞ የአፍጋን ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኻኒ አገሪቱን ጥለው እንደሸሹ ወዲያኑ ነበር፡፡

ጋኻኒም ባላፈው ረቡዕ ለአፍጋኒስታን ህዝብ በፌስቡክ አማካይነት ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል

“ ደመ መፋሰስና የካቡልን ውድመት ለመከላከል፣ ካቡልን ትቼ ለመውጣት ተገድጃለሁ፡፡”

ዩናይትድ ስቴትስ ከአገር የማስወጣቱን እንቅስቃሴ እስከ ነሀሴ 25 ድረስ ለማከናወን ቃል ገብታለች፡፡ ይሁን እንጂ ህይወታቸው አደጋ ላይ የሚገኙትን ሁሉ ለማውጣት ያ በቂ ጊዜ አይመስልም፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ እንዲህ ይላሉ

“ዋናው ጉዳይ እስከተቻለን ጊዜ ድረስ የቻልነውን ያህል እናደርጋለን፡፡ ያለን ጊዜ ሁለት ሳምንታት ብቻ ከሆነ በዚያ ጊዜ ውስጥ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡ ክፍተቱ ከዚያም በላይ ከሆነ በዚያ ክፍተት ውስጥ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡”

ከኤቢሲ ቴሌቪዥን ጆርጅ ስቴፍአናፖልስ ጋር ባላፈው ረቡዕ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባደረጉት ቃለ ምልልስ የአፍጋን ዜጎችን ከዚህ ወር መጨረሻም በኋላ ማውጣት ስለሚቻልበት መንገድ ተስፋ ሰጥተዋል፡፡

ከምልልሱ ተከታዩ ይገኝበታል፡

“ ከነሀሴ 31 በኋላ እንደምናጠናቅቀው አሜሪካውያን ሊረዱት ይገባል፡፡”

ግን ያንን ካላደርግን ወታደሮቻችን በዚያ ይቆያሉ? ጋዜጠኛው ጠየቃቸው

“ያንን ካላደረግን ማን እንደቀረ ለይተን እናውቃለን፡፡”

ከዚያስ በኋላ? አላቸው አሁንም ጋዜጠኛው

“አሜሪካውያን ዜጎቻችን ከቀሩ እነሱን እስክናስወጣ ድረስ እንቆያለን”

መልእክቱ ህይወታቸው አደጋ ላይ ባለና ከአፍጋኒስታን መውጣት በሚገባቸው አፍጋኖች ዘንድ ከፍተኛ መረበሽን ሊፈጥር ይችላል፡፡

አሜሪካውያን አጋሮቻቸውም እነሱን ለማውጣት የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ እየሞከሩ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG