በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታሊባን ኃይሎች ካቡል ገቡ


የታሊባን ኃይሎች ካቡል ገብተዋል
የታሊባን ኃይሎች ካቡል ገብተዋል

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ የአፍጋኒስታን በታሊባን ኃይሎች እጅ መውድቅና የካቡል ውድቀት “ልብ የሚሰብር ነገር ነው” ሲሉ በዛሬው እለት ተናግረዋል፡፡

ሁሉንም አሜሪካውያንን ጨምሮ፣ በአፍጋኒስታን፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ሲሰሩ የቆዩ፣ የአፍጋኒስታን ዜጎችን በሙሉ፣ ከአገር ለማውጣት የአሜሪካ ኃይሎች እየሠሩ ነውም ብለዋል፡፡

“ዋሽንግተን፣ ለአፍጋኒስታን ውድቀት ዝግጁ አልነበረችም” ለሚለው ትችት፣ በሰጡት ምላሽ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣አሁን ድረስ በኤምባሲው የሚገኙ አንዳንድ የአሜሪካ ሠራተኞችና ረዳቶቻቸው የሆኑት የአፍጋን ዜጎች ደህንነት፣ ቅድሚያ የሰጠነው “ቁጥር አንድ ሥራችን” ብለዋል፡፡

ብሊንክን ዛሬ ለሴኤን ኤን በሰጡት መግለጫቸው፡ “እኛ ታሊባኖችን ምንም ነገር አልጠየቅናቸውም” ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ ይሁን እንጂ ግን ሠራተኞቻችን ለማውጣት ወይም ከዚህ ተያይዞ በምናደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ ጣልቃ የሚገቡ ከሆነ እጅግ ፈጣንና ወሳኝ የሆነ እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ትናንት በካቡል የአሜሪካን ይዞታዎች ለማስጠበቅና አሜሪካውያን እና የአፍጋን ረዳቶቻቸውን ለማስወጣት 1ሺ ድጋፍ ሰጭ ወታደሮችን ወደ ካቡል መላከቸውን አስታውቀዋል፡፡

በሌላም በኩል የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋሃኒ፣ ም/ፕሬዚዳንታቸው እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው በዛሬው እለት አገር ለቀው መውጣታቸው ታውቋል፡፡

ባለሥልጣናቱ ላለፉት 20 ዓመታት በዩናይትድ ስቴትስ መሪነት በተሰማራው ጦር በተወገዱትና ዛሬ ወደ ሥልጣን ለተመለሱት የታሊባን ኃይሎች አገሪቱን ትተው መውጣታቸውም ተመልክቷል፡፡

የታሊባን ኃይሎች ወደ ዋናው ከተማ ካቡል በመድረስ መላውን አፍጋኒስታን የተቆጣጠሩት በተለይ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ባደረጉዋቸው ተከታታይ ጥቃቶች ነው፡፡

ለዚህና ለሌችም የእለቱ ዋና ዋና ዜናዎች የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ

የታሊባን ኃይሎች ካቡል ገቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:01 0:00


XS
SM
MD
LG