በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታኑ ቀውስ ምዕራባውያን መሪዎችም ተተችተዋል


የዩናይትድ ስቴትስ ማሪን ወታደሮች ከአፍጋኒስታን ለቀው የሚወጡ ዜጎችን ሲጠብቁ ሀሚድ ካርዛይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ካቡል
የዩናይትድ ስቴትስ ማሪን ወታደሮች ከአፍጋኒስታን ለቀው የሚወጡ ዜጎችን ሲጠብቁ ሀሚድ ካርዛይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ካቡል

በአፍጋኒስታን ቀውስ የታሊባንን ፈጣን ጥቃት አስመልከቶ፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ብቻ ሳይሆኑ የአውሮፓ መሪዎችና የደህንነት አማካሪዎቻቸው ጭምር የተሳሳተ ግምት የነበራቸው በመሆኑ የሚደርስባቸው የትችት ናዳ እየጨመረ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እና ከፍተኛ አማካሪዎቻቸው ከራሳቸው ወገን ከሆኑ የህግ አውጭዎችና ከተቃዋሚ የፖለቲካ ሰዎች ትችት ቀርቦባቸዋል፡፡

የጠቅላይ ሚንስትሩ ወግ አጥባቂ ፓርቲ አባልና የቀድሞ የእንግሊዝ መከላከላይ ሚኒስትር የነበሩት ቶቢያስ ኤልውድ “ መጀመሪያ ከአገር የምታስወጣው ወታደሮችን ሳይሆን ሰለማዊ ዜጎችን ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ነው አንተ ማፈግፈግ የማትጀምረው” በማለት በአውሮፓና በኔቶ መሪዎች መካከል የነበረውን ቅንጅትና ግምት ጨምረው ነቅፈዋል፡፡

ትችቱ የዩናይትድ ስቴትስ እና የኔቶ አባል አገሮች የታሊባንን እርምጃ አስቀድመው በማወቅ የሚወጡበትን መንገድ ማቀድ ነበረባቸው የሚል ነው፡፡

በፕሬዚዳንት ባይደን ጦራቸውን ከአፍጋኒስታን ለማውጣት ከወሰኑ በኋላ ለተሰራው ስህተት አገር መሪዎችም መተቸታቸው ተነግሯል፡፡ የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ኔቶ አባል

በጀርመንም እንዲሁ የፕሬዚዳንት አንጄላ መርኬል መንግሥት ታሊባኖቹ ካቡልን ከመቆጣጠራቸው በፊት ለቆ የመውጣቱን ሂደት ባለማጠናቀቁ ትችቱ ዘንቦበታል፡፡ የጀርመኖች ወታደሮችን በመርዳት አብረው ሲሰሩ የነበሩ 50ሺ የሚደርሱ የአፍጋኒስታን ዜጎችም እጣ ፈንታም በጀመርን እያነጋገር መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ልክ እንደ አሜሪካውያን ሁሉ የአውሮፓ የመረጃና ደህንነት ተቋማትም ታሊባኖች አፍጋኒስታንን ከመቆጣጠራቸው በፊት ለቆ ለመውጣት የሚያስችል ብዙ ጊዜ ያላቸው መስሏቸው ነበር የሚል ትችት ቀርቦባቸዋል፡፡

ታሊባኖች ከቀናት በፊት ቀደም ሲል የነበራቸውን እቅድ አስመልከቶ የነበራቸውን መረጃ አለመጠቀማቸውም በተለያዩ የመገናኛብዙሃን የቀረቡ የደህንነትና ወታደራዊ ባለሙያዎች ምክሮችንም አለማድመጣቸው ተገልጿል፡፡

በሌላም በኩል ዛሬ ሰኞ በአፍጋኒስታን ካቡል አውሮፕላን ማረፊያ በስተሰሜን በኩል ባለው መግቢያ ላይ፣ ማንነቱ ባልታቀ ኃይል የተኩስ ጥቃት የተሰነዘረ ሲሆን አንድ የአፍጋን የጸጥታ ሠራተኛ ሲገደል ሌሎች ሶስት ሰዎች መቁሰላቸውን የጀመርን ጦር አስታውቋል፡፡

በሌላም በኩል በካቡል የአውሮፕላን ማረፊያ የሚታየው መጨናነቅ እየጨመረ ባለበት ሰዓት አፍጋኒስታንን ለቀው መሄድ የሚፈልጉ አሜሪካውያን ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ እንደሚያስወጣቸው የባይደን አስተዳደር ቃል ገብቷል።

አሜሪካኖችንና አጋር የአፍጋን ዜጎችን የማስወጣቱ ሂደት እሁድ እለትም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን የንግድ አውሮፕላኖች ሂደቱን እንዲያግዙ ዩናይትድ ስቴትስ ትዕዛዝ አስተላልፋለች።

ቀሪውን ዘገባ ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በአፍጋኒስታኑ ቀውስ ምዕራባውያን መሪዎችም ተተችተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:20 0:00


XS
SM
MD
LG