በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍጋኒስታንን ለቆ በመውጣቱ ግርግር 7 ሰዎች ሞቱ


ከአፍጋኒስታን ለመውጣት ከካቡል አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚጠባበቁ ሰዎች (ፎቶ ኤ ኤፍፒ)
ከአፍጋኒስታን ለመውጣት ከካቡል አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚጠባበቁ ሰዎች (ፎቶ ኤ ኤፍፒ)

አፍጋኒስታንን ለቀው ለመውጣት፣ በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ከሚራኮቱት፣ በሺዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች መካከል፣ በትናንትናው እለት 7 ሰዎች መሞታቸውን የእንግሊዝ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ ዛሬ እሁድ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ታሊባኖች አፍጋኒስታንን ከተቆጣጠሩ 10 ቀናት ሆኗቸዋል፡፡ በቀድሞ የ20 ዓመት የአስተዳደር ዘመናቸው የነበረውን፣ ጥብቅ የእስላማዊ ህግ የአገዛዝ ሥርዓታቸውን መልሰው ሊያመጡ ይችላሉ፣ በሚል ስጋት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ አፍጋኒስታንን ለቀው ለመውጣት እየተራኮቱ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የእንግሊዝ መከላከያ ሚኒስቴር በመግለጫው “አሁን ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢና ፈታኝ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተቻለ መጠን በሰላምና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እንዲከናወን የተቻለን ሁሉ እያደረግን ነው” ብሏል፡፡

ሮይተርስ በስፍራው የነበረውን የስካይ ኒውስ ዘጋቢ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሰባቱ ሰዎች የሞቱት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ በፈጠሩት ግፊያ፣ ከፊት የነበሩት ሰዎች ለከለላ ከተጋረጡ ግድግዳና ወለሎች ጋር በመላተማቸው ነው ብሏል፡፡

በሌላም በኩል በአፍጋኒስታን የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አገር ለቀው መውጣት የሚፈልጉት ዜጎች ከኤምባሴው በየግላቸው ትዕዛዝ ካልደረሳቸው በስተቀር ወደ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዳይሄዱ በትላንትናው እለት ማስጠንቀቂያ ማውጣቱን አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ማስጠንቀቂያው በዜጎች ላይ ሌላ ስጋትና ግራ መጋባት መፍጠሩ ተመልክቷል፡፡

ታሊባን ደግሞ ዛሬ እሁድ ባወጣው መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስን ተጠያቂ አድርጓል፡፡

የታሊባን ከፍተኛ ባለሥጣልን አሚር ካኻን ሙታቂ ዛሬ ባወጡት መግለጫ “በመላ አገሪቱ ሰለምና መረጋጋት ያለ ሲሆን ግርግሩ ያለው በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ብቻ ነው” ብለዋል፡፡

“አሜሪካ ያላትን ሙሉ አቅሟንና ችሎታዋን የተጠቀመች፣ ፕሬዚዳንቱም ለቆ ስለመውጣቱ ሂደት በቀጥታ ትኩረታቸውን የሰጡት ቢሆንም፣ በአውሮፕላን ማረፊያ ላይ ግን ሥርዓት ማስከበር አልቻሉም” ሲሉ አሜሪካን ኮንነዋል፡፡

የአይን እማኞች ደግሞ ታሊባኖቹ በአውሮፕላን ማረፊያው አቅራቢያ የተሰበሰቡ ሰዎችን ለመበተን ጥይቶችን ወደላይ እንደሚተኩሱ ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስት አንተኒ ብሊንከን ዛሬ እሁድ ከፋክስ ቴሊቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ በአውሮፕላን ማረፊያ ያለው ሁኔታ እጅግ አደገኛና ተለዋዋጭ መሆኑን ገልጸው ይሁን እንጂ ዩናትድ ስቴትስ ባላፉት 24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 7ሺ400 ሰዎችን ከካቡል ማውጣቷን አስረድተዋል፡፡

ዋይት ሀውስም በሰጠው መግለጫ አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ብቻ ወደ 25ሺ 100 ሰዎችን ማውጣት መቻሏን ገልጸው ከሀምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ እስካሁን በጠቅላላው 30ሺ ሰዎችን ማውጣት መቻሉን አስታውቋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በዛሬው እለት በአፍጋኒስታን ስላለው ሁኔታ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋያል ያድምጡ፡፡

አፍጋኒስታንን ለቆ በመውጣቱ ግርግር 7 ሰዎች ሞቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:27 0:00


XS
SM
MD
LG