በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍጋኒስታኑ ቀውስ በአፍሪካም አስተጋብቷል


ፈረንሳይ ከማሊ ወታደሮች ጋር የነበራትን የጋራ ወታደራዊ ዘመቻ አቋርጣለች፡፡ የፈረንሳይ ወታደሮች ለአራት ወራት በሳህል የነበራቸውን ወታደራዊ ዘመቻ እና የጋዎ ጦር ሠፈር ለቀው ሲወጡ፡፡ እኤአ ሰኔ 9 2021
ፈረንሳይ ከማሊ ወታደሮች ጋር የነበራትን የጋራ ወታደራዊ ዘመቻ አቋርጣለች፡፡ የፈረንሳይ ወታደሮች ለአራት ወራት በሳህል የነበራቸውን ወታደራዊ ዘመቻ እና የጋዎ ጦር ሠፈር ለቀው ሲወጡ፡፡ እኤአ ሰኔ 9 2021

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች፣ አፍጋኒስታንን ለቆ የመውጣቱ ውሳኔ ያስከተለው ምስቅልቅል፣ በሺዎች ኪሎሜትር ርቃ በምትገኘው የአፍሪካዋ ሳህልም እንዳይደገም ስጋት መፍጠሩ ተዘግቧል፡፡

ስጋቱ የመጣው ሌላኛዋ ኃያል አገር ፈረንሳይ፣ በአፍሪካው ሳህል፣ የጀመረችውን የረጀም ጊዜ የጸረ ሽብር ዘመቻ ለማቋረጥ በማሰቧ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ፈረንሳይ የጸረ ሽብር ዘመቻውን ቢያንስ አሁን ባለበት ደረጃ መቀጠል አለመፈለጓን አስታውቃለች፡፡

አፍሪካ ውስጥ፣ ሰፊ አካባቢን በሚያካልሉት በኒጀር፣ ቡርኪና ፋሶና ማሊ ድንበሮች አካባቢ፣ በርካታ የእስላማዊ ኃይሎች ጥቃቶች እየሰነዘሩ ነው፡፡

በጥቃቶቹም በርካታ ሰላማዊ ዜጎችና ወታደሮች እየተገደሉ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

በአንዳንዶች ተንታኞች ዘንድ፣ ይህም እንደ አፍጋኒስታኑ ሊያሸንፉት የማይችሉት ጦርነት መሆኑ የተነገረለት ሲሆን፣ አካባቢው እጅግ የተራዘመ ጦርነት የተካሄደበት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱበት፣ ከ2ሚሊዮን በላይ ህዝብ የተፈናቀሉበት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ተንታኞች በሁለቱም ጦርነቶች መካከል ልዩነት ቢኖርም በርካታ ተመሳሳይ ነገሮች መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡

ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የአፍጋኒስታኑ ቀውስ በአፍሪካም አስተጋብቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:14 0:00

XS
SM
MD
LG