በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአል-ሸባብ መዳከምና አዲስ የጥቃት ስልት


የአል-ሸባብ ታጣቂ
የአል-ሸባብ ታጣቂ

ወደ 50 በሚሆኑ የስዋሂሊ ቋንቋ ተዋጊዎች የታጀበ አንድ ጥቁር መለያ የለበሰ የነውጠኛው ቡድን አባል፣ በ21 ደቂቃ የቪዲዮ መልዕክቱ፣ በእርግጥም የአል-ሸባብ ተዋጊዎች ቁጥር እየመነመነ መሄዱን ይፋ አድርጓል።

የሶማልያ የደኅንነት ባለሥልጣናት በሚሰለጥኑበት በአንድ የሞቅዲሾ ወታደራዊ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለደረሰ ጥቃት፣ አል-ሸባብ ባለፈው ሰኔ ወር ኃላፊነት መውሰዱ ይታወሳል።

ነውጠኞቹ ከዚህም ሌላ፣ ደቡባዊ ሶማልያ ውስጥ በሚገኘው ቡሩንዲያውያን የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት ላይ ጥቃት አካሂደው ፴ ወታደሮችን ገድለዋል። የኬንያ የደኅንነት ኃይሎች በቅርቡ፣ እስከ ሶማልያ ድንበር በምትዋሰነው በኬንያዋ ቦኒ (Boni) ጫካ ውስጥ የመሸገውን አል-ሻባብ ለለማባረር አንድ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ አካሂደው እንደነበር ይታወቃል።

የኬንያው አል-ሻባብ ጦር አዛዥ በበኩሉ፣ ረዥም ለሆነ ውጊያ እየተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጿል።

ከአል-ቃዒዳ ጋር ንክኪ ያለው አል-ሻባብ፣ ዓለማቀፍ ድጋፍ የሚያገኘውንና የሞቅዲሾ ውጥ ያለውን መንግሥት ለመገልበጥ የሚዋጋ ቡድን መሆኑ ይታወቃል። የሶማልያው መንግሥት ከኬንያ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከቡሩንዲ፣ ከኡጋንዳና ከጁቢቲ በተውጣጡ በ22,000 ወታደሮች ይታገዛል።

አዲሱ አበበ አጠናቅሮ ያዘጋጀውን ሙሉውን ዝርዝር ለመስማት የተያያዘውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የአል-ሸባብ መዳከምና አዲስ የጥቃት ስልት /ርዝመት - 4ደ19ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:19 0:00

XS
SM
MD
LG