በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ መንግሥት የአል-ሽባብን የጥቃት ሴራ በብዛት አክሽፈናል አለ


የአል-ሸባብ ታጣቂ
የአል-ሸባብ ታጣቂ

እአአ ከ 2014 ዓም ወዲህ የሶማሊያው ጽንፈኛ ቡድን የአል-ሸባብ የሽብር ጥቃት በስድሳ ከመቶ መቀነሱን ዋናው የሀገሪቱ የብሄራዊ ስለላ አገልግሎቶች ሃላፊ ገለጹ።

ጄኔራል አብዲራህማን ቱርያሬ ለአሜሪካ ድምጽ የሶማሊኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል መጠይቅ ከሽብርተኛው ቡድን አሁንም ተጨባጭ ስጋት መኖሩን አምነው የሀገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች በህዝባዊ ስፍራዎች አጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶችን ፍንዳታዎችን ለመከላከል በሚረዱ ቴክኖሎጂዎች መጠቀም ይኖርባቸዋል ብለዋል።
“የደህንነት ኣገልግሎታችን ያከናወናቸውን ትልልቅ ተግባራት አንዳንዱን ለመጥቀስ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ አልሸባብ ህዝባዊ ስፍራዎች ላይ ለማድረስ የነበሩ ሁለት መቶ ዘጠኝ የጥቃት ሴራዎች በባለስልጣናት ላይ ግድያ ለመፈጸም ያቀዳቸውን በርካታ ዕቅዶች አክሽፈዋል" ሲሉ ጄነራል ኣብዲራህማና ቱሪያሬ ገልጸዋል።
የሶማሊያ የፀጥታ ሚኒስቴርና የብሄራዊ ደህንነት መስሪያ ቤቶቹ ንጹሃንን ለመግደል የሚሩዋሩውጡት ሽብርተኞች የሚሰነዝሩትን ጥቃት በሙሉ ለመዋጋትና ለማክሸፍ አዲስ ዕቅድ የሚያወጡ መሆኑን የብሄራዊ ደህንነቱ ባለስልጣን አመልክተዋል። ከሚካሄዱት ጥረቶች ውስጥ ህዝቡ ስለእስልምና ሃይማኖት ያለውን ግንዛቤና ዕውቀት ማሳደግ መሆኑን የተናገሩት የሶማሊያው ባለስልጣን ጽንፈኝነት ለመከላከል በሚደረጉት ጥረቶች የሀገሪቱ ምሁራን እንደሚሳተፉ ነው ያስረዱት።
የመንግስቱ ዋና የደህንነት ሃላፊ እንዳሉት አል-ሸባብ እንደሆቴል እና ምግብ ቤት በመሳሰሉ ህዝባዊ ስፍራዎች የሚያደርሰው ጥቃት ከሶማሊያ ወታደሮች ጋር መዋጋት እያቃተው መምጣቱን በግልጽ የሚያሳይ ነው ።
ሙሉውን ዝርዝር ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
የሶማሊያ መንግሥት የአል-ሽባብን የጥቃት ሴራ በብዛት አክሽፈናል አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:49 0:00

XS
SM
MD
LG