ዋሽንግተን ዲሲ —
የሱዳኑ ወታደራዊ አዛዥ ጀነራል አብደልፋታህ አል ቡርሃን የጦር ሠራዊቱ የሽግግሩን መንግሥት የገለበጠው “የርስ በርስ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ለመከላከል ነው” ብለዋል።
በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ተለቅቀው ቤታቸው ገብተዋል።
በሌላ በኩል የአፍሪካ ኅብረት ሱዳንን በማናቸውም የኅብረቱ እንቅስቃሴ እንዳትሳተፍ አግዷል።
የዐለም ባንክ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ገልፆ ለሱዳን የሚደረጉ የገንዘብ ድጋፎችን ለጊዜው ማቆሙን ሲል አስታውቋል።
በቪኦኤ ዘጋቢዎች የተጠናቀሩና ሌሎችም የዜና ወኪሎች ያሠራጯቸውን ሪፖርቶች ቆንጅት ታየ እንደሚከተለው አቀናጅታቸዋለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡