በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጀኔራሉ "ወታደራዊ ግልበጣው እርስ በርስ ጦርነትን ለማስወገድ ነው" አሉ


የሱዳን ወታደራዊ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታ አልቡርሃን
የሱዳን ወታደራዊ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታ አልቡርሃን

የሱዳን ወታደራዊ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታ አልቡርሃን “የሽግግሩን መንግሥቱን መገልበጥ የእርስ በርስ ጦርነትን ለማስወገድ አስፈላጊ ነበር” ሲሉ ትናንት ማክሰኞ በቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ተናገሩ፡፡

"መላው አገሪቱ በተቃናቃኞች ፖለቲካ ተይዛ መንቀሳቀስ አልቻለችም" ያሉት አልቡርሃን "ባላፉት ሁለት ዓመታት ሽግግር ውስጥ የታየው የፖለቲካ ኃይሎች ተሳትፎ ጉድለት የተሞላበትና ግጭት የሚያነሳሳ ነበር" ብለዋል፡፡

ባለፈው ሰኞ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክና ባለቤታቸው በጥብቅ ክትትል ስር መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ትናንት ማምሻውን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መደረጋቸውም ተዘግቧል፡፡

“ሚኒስትሮችና ፖለቲከኞችን በቁጥጥር ስር አውለናል” በማለት እስሩን ያረጋገጡት ቡርሃን “ያስረነው ግን ሁሉንም አይደለም” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከክን የሀምዶክ መለቀቅ አድንቀው ከሀምዶክም ጋር ማምሻውን መነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡

ብሊንክን የሱዳን ወታደሮች ሌሎች የሲቪል መሪዎችንም እንዲለቁ ባወጡት መግለጫ አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG