በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የጸጥታ ምክር ቤት በሱዳን ጉዳይ ይመክራል


ተቃዋሚ ሰልፈኞች ካርቱም፤ ሱዳን
ተቃዋሚ ሰልፈኞች ካርቱም፤ ሱዳን

የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በሱዳን የሽግግር መንግሥት ላይ በተደረገው ወታደራዊ ግልበጣ ጉዳይ ዛሬ ማክሰኞ በዝግ ተገናኝቶ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዟል፡፡

ትናንት በቁጥጥር ስር የዋሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክና ሌሎች የልዕልና ምክር ቤት ባለሥልጣናትን እስር የተቃወሙ ሰልፈኞች አሁንም በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም አውራ ጎዳናዎች ላይ ይገኛሉ፡፡

ተቃዋሚ ሰልፈኞች ትናንት ምሽቱን ድረስ ያሰሙትን ተቃውሞ ለመበተን የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እምርጃ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን ቢያንስ 80 ሰዎች መቁሰላቸውን የሱዳን የዶክተሮች ኮሚቴ አስታውቋል።

ወታደራዊ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታ አል ቡርሃን በትናንትናው እለት ግልበጣው ከተካሄደ በኋላ፣ የወታደራዊውና የሲቪል አስታዳደሩ የጋራ ምክር ቤት መበተኑን ገልጸው በአገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ የተቋቋመው እኤአ ነሀሴ 2019 የቀድሞ አምባገነን መሪ ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር በህዝባዊ አመጽ ከተወገዱ አጭር ጊዜ በኋላ ነው፡፡

ወታደራዊ ግልበጣውን በመቃወም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ዩናይትድስ ስቴትስን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተቃውሞውን በማሰማት ላይ ይገኛል፡፡

XS
SM
MD
LG