ከ6 መቶ 50 በላይ የአፍሪካ ስደተኞች በደቡባዊ የመን ባህር ጠረፍ ላይ በምትገኘው አደን ከተማ በርሃብና በውሃ ጥም በመሰረታዊ ፍላጎቶች እጦት በእስር እየተሰቃዩ ነው፡፡ እነዚሁ ተስፋ የቆረጡ፣ የተራቡና የተጨነቁ አፍሪካውያን ስደተኞች በደቡባዊ የመን በአድን ከተማ /መጋዘን/ በሚመስል እስር ቤት ውስጥ ተከማችተዋል፡፡ አብዛኞቹ ከአፍሪካ ቀንድ የተሰደዱና ተስፋ የቆረጡ፣ አድካሚና አስልቺ ጉዞ አድርገው አሁን ያሉበት ስፍራ የደረሱ ናቸው፡፡
ዓለምቀፍ የሴቶች ታሪክ ወር በሚታሰብበት መጋቢት - የኢትዮጵያ ሴቶች ስለ ፆታ ዕኩልነት ይናገራሉ
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከሮይተርስ የዜና አገልግሎት ጋር ያደረገው ቃለምልልስ
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያለፈውን የአውሮፓውያኑን 2017 ዓ.ም የሃገሮች ዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሪፖርቱን አውጥቷል። ቁጥራቸው ወደ 160 የሚጠጉ ሃገሮች ተፈፅመዋል ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን በዘገበበት ሪፖርቱ እጅግ ገናና በሆኑ አንዳንድ የዓለም መሪዎች ጥላቻ እና ፍርሃት የነገሰበት የፖለቲካ አሰራር የተለመደ እንዲሆን አድርገውታል ብለዋታል።
ኢትዮጵያ “ሰላማዊ ነች፤ ተቋማቷም ሥራቸውን ያለምንም ችግር እያከናወኑ ናቸው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ለውጭ ሃገሮች ዲፕሎማቶች ተናግረዋል። የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አሿሿምም “በጣም በተሳለጠ ሁኔታ እየተካሄደ” መሆኑን ዶ/ር ወርቅነህ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ለስድስት ወራት ተግባራዊ እንደሚደረግ ለጋዜጠኞች የሰጡት መግለጫ
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ለስድስት ወራት ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሣ ገለፁ። አዋጁ ለመጭዎቹ ስድስት ወራት ተግባራዊ ሆኖ የሚቆየው በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ እንደሚሆንና በሁሉም አካባቢዎች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ አመልክተዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለስድስት ወራት እንደሚቆይ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ሲልፁ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡ፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሥራ መልቀቂያ ባስገቡ ወቅቱ የሰጡት መግለጫ
የኢትዮጵያ የወቅቱ ሁኔታ የማይቆም የለውጥ ሂደት ላይ እንደሚገኝ የገለፁት የኢትዮጵያ የኮምዩኒኬሽንስ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ኢትዮጵያዊያን ለውጡን በመደገፍ አብረው እንዲቆሙ ጠይቀዋል። ያ ለውጥ ምንድነው? ወደ የትስ ይወስዳት ይሆን? ለምን ይሆን መንግሥት በሰላማዊ ሕዝብ መካከል የታጠቀ ኃይል የሚያሰማራውና ወታደሮቹ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተው እንዲገድሉ ባለሥልጣናቱ ትዕዛዝ የሚሰጡት? ለጠፋው ሕይወት የሚጠየቅስ ይኖር ይሆን?
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለመነሳት መልቀቂያ ማስገባታቸው ተገለፀ፡፡
እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ አሕመድ ሙስጠፋ፣ አሕመዲን ጀበልና ሌሎች እስረኞች ዛሬ አመሻሹ ላይ ሲፈቱ በርካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በመገኘት ደስታውን ሲገልፁ ነበር፡፡
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በትናንትናው ዕለት ከእሥር ሲፈቱ በሀገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች የደስታ መግለጫ ሰልፎች እንደነበረ ሲገለፅ አብዛኞቹ በኦሮምያ ክልል ናቸው፡፡ የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ከእስር ከወጡ በኋላ ወደ አዳማ መኖሪያ ቤታቸው ሲያመሩ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በየጎዳናው በመውጣት፣ በተሽከርካሪዎች በማጀብ አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡
ከመንግሥት ሰራተኞችና ከሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች እያገኙት ያለው ድጋፍ የሕዝቡ ትግል አንድ እርምጃ ወደ ፊት መሄዱን እንደሚያሳይ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል፡፡
ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ዛሬ ዓርብ የተከፈተው የክረምት ኦሎምፒክስ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከትናንት በስተያ ለተወካዮች ምክር ቤቱ ጥምር ጉባዔ ያደረጉት ንግግር በተከታተሉት አሜሪካዊያን በአመዛኙ አዎንታዊ አቀባበል ማግኘቱ እየተሰማ ነው። ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ላይ መተባበርና የሁለቱንም ገዥ ፓርቲዎች የጋራ ውሣኔዎች መጠየቃቸው ብዙ ሪፐብሊካንን አስደስቷል።ዴሞክራቶቹ ግን በትረምፕ እውነተኛ አቋም ላይ ጥርጣሬአቸው እንደበረታ ነው።
የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደትን በሚያደናቅፉ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ጊዜው አሁን ነው ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ አስታወቁ፡፡ የሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ አዲስ አበባ ላይ ተከፍቷል፡፡
ላለፉት 18 ዓመታት አንድ ሥራ ላይ ያለ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በዓለም የምጣኔ ኃብት መድረክ ላይ ሲሣተፍ የአሁኑ የመጀመሪያው ሊሆን ነው። Davos Elite Brace for Trump’s ‘America First’ Agenda
ሙስና በአፍሪካ ውስጥ እያስከተለ ያለው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ጣልያን አገር ውስጥ ከሚላን ከተማ ወጣ ብሎ አንድ ባቡር ተገልብጦ ሦስት ሰዎች ሞተው ሌሎች አሥር በጠና መቁሰላቸው ታወቀ። አደጋው ዛሬ ሐሙስ የደረሰው፣ ከሴርሞና ከተማ ወደ ሚላን ያመራ በነበረው የመንገደኞች ባቡር ላይ ሲሆን፣ ሰገሬት ከተማ ሲቃረብ ነው የመካከለኞቹ ፉርጎዎች ከሀዲዱ ሊወጡና ሊገለበጥ የቻለው። የአደጋ መከላከልና አስወጋጅ ቡድን ወደ ስፍራው በመሄድ ለቆሰሉት መንገደኞች እርዳታ ማድረጉም ታውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ