የዚህ ዓመቱ የመሪዎች ጉባዔ በሙስና ላይ ማተኮሩ ትግሉ አሁን ተጀመረ ማለት እንዳልሆነ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ አስታወቁ፡፡
የፈረንሣይ የዜና ወኪል [አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ - ኤኤፍፒ] ስለቴዲ አፍሮ ሰሞኑን አንድ ዘጋቢ ፊልም አውጥቷል።
እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ በተለይም በኒው ዮርኩ ታይም ስኴር ተብሎ በሚታወቀው አደባባይ፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያንና የሌላም አገር ዜጎች፣ እጅግ ኃይለኛ የነበረው የወቅቱ ብርድ ሳይበግራቸው፣ መንፈቀ ሌሊት ላይ 2018ን ተቀብለዋል። የአዲስ ዓመት መግቢያ በኒው ዮርኩ ታይም ስኴር ሲከበር፣ 118 ዓመት ሆኖታል።
ግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ አቅራቢያ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ዛሬ ዓርብ ተኩስ የከፈተው ታጣቂ ቢያንስ አራት ሰዎች ገደለ። ሌሎች አምስት ሰዎች አቁስሏል። ከሞቱት መካከል አንዱ ፖሊስ መሆኑ ታውቋል።
በኅዳሴ ግድብ ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን ወደፊት ለማራመድ የሚያስችል አዲስ ሃሣብ ማቅረባቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ ጉብኝት ላይ ያሉት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰምሃ ሹክሪ አስታውቀዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነው ብለው በዓለም ዙሪያ ብዙ ክርስትያን ምዕመናን የሚያምኑበት የዛሬው የገና በዓል በፍልስጥዔማዊያን ይዞታ ሥር ባለችው ቤተልሄም እየተከበረ ይገኛል።
የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ፣ በኢየሩሳሌእም ሰላም፣ በኮሪያው ባሐረ ገብ መሬትም መረጋጋት ይሆን ዘንድ ጥሪ አሰሙ። አቡኑ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ዛሬ እየተከበረ ያለውን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ነው፣ ለኢየሩሳሌምና ለመላው ዓለም በሚል ቃለ ምዕዳንና ጥሪያቸውን ያቀረቡት።
ዩናይትድ ስቴትስ እየሩሳሌምን በእሥራኤል ዋና ከተማናት በመቀበል ዕውቅና ሰጥታ ኤምባሲዋን ወደዛው ለማዛወር የደረሰችበትን አቋም የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ በከፍተኛ የድምፅ ብልጫ የተቃውሞ ውሳኔ አሳልፎበታል፡፡
ከሁለት ዓመታት በፊት የተፈረመው የደቡብ ሱዳን የሰላም ሥምምነት እንዲተገበር የተቀናጀ ግፊት የሚያደርግ ስብሰባ ዛሬ በአፍሪካ ሕብረት ተጀምሯል፡፡
ይህ ምርጫ ታዲያ ቀጣዩ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማን እንደሚሆን ፍንጭ የሚሰጥ እንደሚሆን ብዙዎች ያምናሉ። ቁጥራቸው ወደ አምስት መቶ የሚጠጋ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲው አባላት ጆሃንስበርግ ወስጥ ድምፃቸውን ሊሰጡ የታቀደው ትናንት እሁድ እንደነበር ሆኖም ሂደቱ መዘግየቱ ነው የተገለጠው።
ዩናይትድ ስቴትስ ካሉባት የበረቱ ፈተናዎች አንዱ በወል መጠሪያ ‘ኦፒዮይድስ’ የሚባሉ አደንዛዥና ሕመም አስታጋሽ መድኃኒቶች ሥር የሰደደ ቀውስ ነው።
መሻሻል ባለባቸውና ልዩነት በፈጠሩ ጉዳዮች ላይ ሃገራቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በግል ስትወያይ መቆየቷን፣ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ተናገሩ።
በያዝነው ወር በሚያበቃው 2017 ምሥራቅ አፍሪካ ላይ በተከሰተው አስከፊ ድርቅና ግጭት ምክንያት ከ37 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከባድ የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል።
በትልቅነቱ ከዓለም አሥራ አራተኛ የሆነው እና ሲየራሊዮን ውስጥ የተገኘው አልማዝ ኒው ዮርክ ላይ ከሥድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሸጠ፡፡ ሴራሊዮን ከአልማዙ ሽያጭ የተገኘው ገንዘብ ለልማት ዕቅዶች ማካሄጃ ይውላል ብላለች። ሀገሪቱ ባለሰባት መቶ ዘጠኝ ካራቱን ያልተከርከመ አልማዝ ጨረታ ላይ ስታወጣው የአሁኑ ሁለተኛ ጊዜ ነው። ባለፈው ግንቦት ወር ዋና ከተማዋ ፍሪታውን ላይ “ከሠባት ሚሊዮን በላይ ልክፈል ያለ” ተጫራች ቀርቦ አያዋጣኝም ብላ ትታዋለች።
የመን ዋና ከተማ ሳንዓ ውስጥና በአካባቢዋ የቀድሞ አጋሮች በነበሩት የሁጢ አማፂያንና በቀድሞው ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳለህ ታማኝ ኃይሎች መካከል በተቀሰቀሰውና ላለፉት በርካታ ቀናት እየተካሄደ ባለው የከበደ ውጊያ በአሥሮች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው እየተሰማ ነው።
የቀድሞ የየመን ፕሬዚደንት አሊ አብዱላ ሳልህ መገደላቸውን ፓርቲአቸው አረጋገጠ። በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ‘የርሳቸው አስከሬን ነው’ የተባለ ምሥል የያዘ ቪዲዮ እየታየ ነው።
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳት አባ ፍራንሲስ፣ ባንግላዴሽ ዋና ከተማ ውስጥ ከቤት ውጪ ዛሬ በተካሄደ ሰፊ የቅዳሴ ሥነ ስርዓት፣ ለ16 አገልጋዮች ሥልጣነ ክህነት ሰጡ።
ማያንማርን ለአራት ቀናት የጎበኙት የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ፣ ዛሬ ባንግላዴሽ ገቡ። በማያንማሯ ያንጎን ለሚገኙ የካቶሊክ ወጣት ምዕመናን የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት የመሩት አባ ፍራንሲስ ዛሬ ነው፣ ባንግላዴሽ የገቡት።
ሩሲያ በጎረቤቶቿ ላይ በተለይ በምርጫ ሂደቶቻቸው ውስጥ ጣልቃ እየገባች ምስቅልቅል ለመፍጠርና ኢ-ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦችን ለመጫን በተከታታይ ትከተለዋለች ያሉትን ባህርይዋን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን አወገዙ።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሜን ኔታንያሁ ኡሁሩ ኬንያታ 4ኛው የኬንያ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መኃላ በፈጸሙ ወቅት በኬንያ ተገኝተው ነበር፡፡ ነገር ግን በናይሮቢ ካሳራኒ ስታዲዬም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኬንያውያን እና ከ40 በላይ መንግሥታት ተወካዮች በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ ዝግጅቱን አልታደሙም፣ ለሴኩሪቲ ሲባል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ