የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ሥነ ስርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፀመ።
በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ማለዳ በዋሽንግተን ዲሲ የስብሰባ ማዕከል ተሰልፈው ወደ አዳራሽ ለመግባት ሲጠባበቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በውጭ ከሚኖሩ ወገኖቻቸው ጋር በኢትዮጵያ መንግሥትና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መካከል መቀራረብና መተባበር እንዲኖር ያለመ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
በከፍተኛ የእናቶች ሞት ከሚጠቀሱ የዓለም ሃገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት ። ከአስራ ሰባት ነፍሰ ጡር ሴቶች አንዷ በወሊድ ወቅት ህይወቷን ታጣለች። ይህን ለመታደግ ታዲያ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ርቀው ባሉ ገጠራማ ሥፍራዎች የሚኖሩ ነፍሰጡሮች ለራሳቸውም ሆነ ለሚወለደው ህፃን የጤና እንክብካቤ ማግኘት ወደሚችሉባቸው የጤና ጣቢያዎች አቅራቢያ ጠጋ ብለው የሚቀመጡባቸው ማረፊያ ቤቶች እየተሰናዱላቸው ነው።
ኤርትራ በኢትዮጵያ የነበራትንና ከበርካታ ዓመታት በፊት የተዘጋ ኤምባሲዋን ዛሬ ከፈተች።
ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ለመሩት የሉዑካን ቡድን በአዲስ አበባ እጅግ የደመቀ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ ሲገቡ ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የጥበብ ሰዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም አደባባይ በመውጣት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ቆይታ እንደሚያደርጉ፣ የሀዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክን እንደሚጎበኙም ተገልጿል።
ኢትዮትጵያና ኤርትራ የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነት በተመለከተ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሰጡት አስተያየት
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ በአስመራ ታሪካዊ በተባለ ጉብኝት ተገናኝተው የሁለትዮሽ ምክክር ጀምረዋል። እሁድ ማለዳ በአስመራ አየር ማረፊያ የሁለቱ ሀገሮች መሪዎች ሲጨባበጡና ሲተቃቀፉ፤ በሽዎች የተቆጠሩ የአስመራ ነዋሪዎችም በመንገድ ዳር ተኮልኩለው ሲጨፍሩ ታይቷል። አስመራ በኢትዮጵያና ኤርትራ ባንዲራ ደምቃ ታይታለች።
የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ አስመራ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና ነዋሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሜድትራንያን ባህር በጎማ ጀልባዎች ላይ የነበሩ 60 ፍልሰተኞችን ያሳፈረው ስደተኞቹን ከሞት ለማትረፍ የሚጥረው መርከብ ማልታና ኢጣልያ አላስገባ ካሉት በኋላ ትላንት በስፔን ወደብ ገብቷል። በያዝነው አመት በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች በአውሮፓ ጠረፎች ላይ ደርሰዋል። ደቡባዊ የአውሮፓ ሀገሮች ሌሎቹም ሸክሙን ካልተጋሩ በስተቀር በአሁኑ ወቅት የገቡትን ፍልሰተኞች አንቀበልም እያሉ ነው።
35ኛው የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ - ዳላስ ቴክሳስ
ሶፊያ የተባለቸው እና ከሰው ልጅ ቀርፅ ጋር ተመሳስላ የተሰራቸው ሮቦት፣
የባህር ዳር ነዋሪዎች ለጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ በባህር ዳር ስታድዬም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በሰልፍ ላይ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ሲገልፁ።
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አብይ አሕመድ ለኤርትራ መንግሥት ልዑካን ቡድን በብሄራዊ ቤተ መንግሥት የእራት ግብዣ አድርገዋል፡፡
የኤርትራ መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከሃያ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ሁኔታዎችን ለመርመር የመጣው የልዑካን ቡድን የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከፍተኛ አማካሪ የማነ ግብረአብና የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህ የሚገኙበት ነው፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፍ ወደ መስቀል አደባባይ የተመመው ሕዝብ - አዲስ አበባ
በመስቀል አደባባይ ዛሬ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ መከሰቱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ድጋፉን ለመስጠት መስቀል አደባባይ የወጣው ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ የነበረውን ቆይታ የሚያሳይ ቪዲዮ።
ነገ በአዲስ አበባ ከተማ “ዲሞክራሲን እናበርታ” በሚል ቃል በሚካሄደው ግዙፍ የድጋፍ ሰልፍ ከፍተኛ ቁጥር ያለው እንደሚገኝ፣ አስተባባሪዎ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ