እኩለ ሌሊት ላይ በደረሱት ጥቃቶች ሶስት ሲቪሎች እና አምስት የጽንፈኛው ቡድን ተዋጊዎች መገደላቸውን የኪስማዮ ባለስልጣን እና የመንደሩዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ደቡብ ሶማሊያ ውስጥ አዲስ የአየር ጥቃት መካሄዱ ተሰማ። እማኞችና የሶማሊያ ባለስልጣናት ለቪኦኤ እንደተናገሩት በታችኛው ጁባ ክፍለ ግዛት ዮንቶይ በምትባል በአል-ሻባቦች ይዞታ ያለች መንደር በደረሱት የአየር ጥቃቶች ቢያንስ ስምንት ሰዎች ተገድለዋል።
እኩለ ሌሊት ላይ በደረሱት ጥቃቶች ሶስት ሲቪሎች እና አምስት የጽንፈኛው ቡድን ተዋጊዎች መገደላቸውን የኪስማዮ ባለስልጣን እና የመንደሩዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በአየር ጥቃቱ የተገደለ የአል-ሻባብ ከፍተኛ አባል ይኖር እንደሆን የኪስማዩ ባልስልታናት አላወቁም። ይሁን እንጂ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት የጽንፈኛው ቡድን ተዋጊዎች በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ ታይተው ነበር ብለዋል።
የአየር ጥቃቶቹን ያደረሱት አውሮፕላኖች የማን እንደሆኑ አልታወቀም። ሆኖም በቅርብ ጊዜያት የዩናይትድ ስቴትስ እና የኬንያ ወታደራዊ ጀቶች በአካባቢው በተደጋጋሚ ጥቃት ሲያደርሱ መቆየታቸው ይታወቃል።