በጋምቤላ ከ200 በላይ ሰዎችን ገድለው አያሌ ህፃናትን የጠለፉ ለፍርድ ሊቀርቡ ነው ተባለ

  • እስክንድር ፍሬው

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ

ከ200 በላይ ሰዎችን በመግደልና ህፃናትን ጠልፎ በመውሰድ ተጠያቂ የሚሆኑትን የሙርሌ ጎሳ አባላት በስም መለየታቸውን የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር አስታወቁ።

መከላከያ ሚኒስቴር የተጠለፉት ሰዎች ቁጥር 103 መሆናቸውን ሲናገር የጋምቤላ ክልል መንግሥት ግን 125 ናቸው ይላል፡፡ 91 ልጆች ተገኝተው መመለሳቸው ቀደም ሲል ተነግሯል፡፡

ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳ ለፓርላማ አባላት እንዳስታወቁት ሰዎቹ ለፍርድ የሚቀርቡት እዚያው ደቡብ ሱዳን ውስጥ ነው።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በጋምቤላ ከ200 በላይ ሰዎችን ገድለው አያሌ ህፃናትን የጠለፉ ለፍርድ ሊቀርቡ ነው ተባለ