ሶማልያ ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር ግንኙነቷን በማሻሻሏ ትልቅ ስኬት እንዳሳየች አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ገለጸ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል - የሶማልያ ከዲያስፖራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚላከውን ገንዘብ ዳሃብሺል የተባለ ኩባንያ(remittance company) የሶማሊ ሽሊንግ እያቀበለ በሞቃዲሹ ሶማልያ

አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ትናንት በሰጠው መግለጫ መሰረት ሮጀርዮ ዛንዳመላ የአስተዳደር ሁኔታን ማሻሳል፣ የገንዘብ አያያዝንና በገንዘባዊ ዘርፍ ልማት ማዳበር በሚመልከቱ ፖሊሲዎች ላያ አትኩረው ለመነጋገር በናይሮቢ ለሰባት ቀናት ያህል ከሶማልያ ባለስልጣኖች ጋር ተሰብስበዋል።

ሶማልያ ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር ያላት ግንኑነትን በማሻሻል ረገድ ትልቅ ስኬት እንዳሳየች አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ገልጿል።

የአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አርማ

አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ትናንት በተናገረው መሰረት ሮጀርዮ ዛንዳመላ የአስተዳደር ሁኔታን ማሻሳል፣ የገንዘብ አያያዝንና በገንዘባዊ ዘርፍ ልማት ማዳበርን በሚመልከቱ ፖሊሲዎች ላይ አተኩረው ለመነጋገር በናይሮቢ ለሰባት ቀናት ያህል ከሶማልያ ባለስልጣኖች ጋር ተሰብስበዋል።

ሶማልያ ራስዋን መልሳ ለመገንባት እንዲሁም ማህበረሰባዊና የኢኮኖሚ መሰረተ ልማት ለመዘርጋት የምታደርገው ጥረት ውጤት እያሳየ ነው ሲሉ ዛንዳመላ አሞግሰዋል።

ሶማልያ አምና ያስመዘገበችው እድገት በ 3.7 ተገምቷል። ይሁንና የጸጥታ ዋስትና ባለመኖሩና ጦርነት ያሚያስከትለው ውድመት በመቀጠሉ በግብር መሰብሰብና ለህዝቡ አገልግሎት በማቅረብ ተግባር ችግር እንዳለ ዛንዳመላ ጠቁመዋል።

በጁባ ክልል ጂቢል ከተማ በሚገኘው የአል-ሸባብ አምባ ላይ ድብደባ ተካሄደ

በሌላ የሶማልያ ዜና ደግሞ፣ የማን መሆኑ ያልታወቀ አይሮፕላን ትላንት ሌሊት በመካከለኛው ጁባ ክልል ጂቢል ከተማ በሚገኘው የአል-ሸባብ አምባ ላይ ድብደባ እንዳካሄደ ከደቡባዊ ሶማልያ የደረሱ ዘገባዎች ገልጸዋል።

ቢያንስ ስምንት የአል-ሸባብ አማጽያን እንደተገድሉ የሶማልያ ጁባላንድ ባለስልጣኖች ተናግረዋል። ዘገባው ግን በነጻ ምንጭ አልተረጋገጠም።

በአል-ሸባብ ጋራጅ ላይ የተፈጸመው ድብደባ በርካታ ብረት ለበስ መኪኖችን እንደደመሰሰ እማኞች ጠቁምዋል።

በሶማልያ ያለው የአፍሪቃ ህብረት የሰላም ጥበቃ ተልዕኮ ወታደራዊ ሃይሉና የሶማልያ ወታደሮች በታችኛው ሸበሌ ክልል በርካታ የአል-ሸባብ ወታደራዊ አዛዦችን ገድለዋል ሲል ባለፈው ማክሰኞም ጠቁሟል። 6 የአል-ሽባብ ወታደራዊ አዛዦች መገደላቸውን በመግለጫው ገልጿል።