የወንዶቹን ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ሥፍራ የወሰዱትና ታሪክ የሠሩት የኢትዮጵያ ሯጮች ደግሞ፥ ለሚ ብርሃኑ፥ ያለፉት ሁለት ዓመታት ሻምቲዮኑ ሌሊሣ ዴሢሣና ፀጋዬ ናቸው።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በ 120ኛው የቦሰተን ማራቶን በሴቶቹ ተከታትለው በመግባት ያሸነፉት፥ አፀደ ባይሣና ትርፊ ነገሪ ናቸው።
የወንዶቹን ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ሥፍራ የወሰዱትና ታሪክ የሠሩት የኢትዮጵያ ሯጮች ደግሞ፥ ለሚ ብርሃኑ፥ ያለፉት ሁለት ዓመታት ሻምቲዮኑ ሌሊሣ ዴሢሣና ፀጋዬ ናቸው።
አሸናፊዎች አንደኛ የወጣው፥ ዋንጫና $150.000 ሺህ ያሜሪካ ዶላር ሽልማት ወስዷል። ሁለተኛና ሦስተኛ የወጡት ደግሞ ሜዳልያ፥ የ $75 እና የ $40 ሺህ ያሜሪካ ዶላር ቼክ ተቀብለዋል።
በዛሬው የቦስተን ማራቶን ውድድር ላይ፥ ከ 50ዎቹም የዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ግዛቶችና ከ 81 ሀገሮች የመጡ አትሌቶች፥ በጠቅላላው 30 ሺህ ሯጮች ተሳትፈዋል። የፀጥታ ጥበቃው ከመቼውም በበለጠ በሚያይና በማይታይ መልኩ ተጠናክሮ እንደነበር ተዘግቧል።
Your browser doesn’t support HTML5