ከተሣፋሪዎቹ አንድ ሰው መሞቱ ከመነገሩ በስተቀር ሌላ የደረሰ ጉዳት ይኑር አይኑር አልተገለፀም።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ንብረትነቱ ዳሎ የሚባል ኩባንያ የሆነ የመንገደኞች አይሮፕላን ወደ ጅቡቲ ለመብረር ከትናንት በስተያ ማክሰኞ ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ዓለምአቀፍ አየር ጣቢያ እንደተነሣ ለደረሰበት የቦምብ ፍንዳታ ተጠያቂው አልሻባብ የሚባለው ፅንፈኛ የሁከት ቡድን ነው ብለው እንደሚጠረጥሩ የሶማሊያ ባለሥልጣናት ዛሬ አስታውቀዋል።
ከተሣፋሪዎቹ አንድ ሰው መሞቱ ከመነገሩ በስተቀር ሌላ የደረሰ ጉዳት ይኑር አይኑር አልተገለፀም።
በአይሮፕላኑ ላይ የነበሩ ሰማንያ አንድ ተሣፋሪዎች አብራሪውና የበረራ ቡድኑ አባላት ለተፈጠረው አደጋ ለሰጡት ምላሽ አሞግሰዋቸዋል። አይሮፕላኑ በተነሣ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ የደረሰው ፍንዳታ በአይሮፕላኑ ጎን ላይ ትልቅ ሽንቁር የከፈተ ሲሆን አብራሪው ወዲያው ወደ አየር ማረፊያው ተመልሶ አይሮፕላኑን አሳርፎታል። የፍንዳታው መንስዔ ምርመራ መቀጠሉም ተገልጿል።
በተጨማሪ ከዚህ በታች ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ።
Your browser doesn’t support HTML5