በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወልቃይት ኮሚቴ አባል ጠፉ


የወልቃይት ካርታ
የወልቃይት ካርታ

በምዕራብ ትግራይ ዞን ወልቃይት አካባቢ ከተነሣው የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ ማዋከብ እየደረሰብን ነው ያሉ የጠገዴ ቀራቅር ነዋሪዎች ዛሬ ሰላማዊ ሠልፍ ማደረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

በምዕራብ ትግራይ ዞን ወልቃይት አካባቢ ከተነሣው የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ ማዋከብ እየደረሰብን ነው ያሉ የጠገዴ ቀራቅር ነዋሪዎች ዛሬ ሰላማዊ ሠልፍ ማደረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

የአካባቢውን ሰዎች የማንነት ጥያቄ ይዞ ወደ አዲስ አበባ ተጉዞ የነበረው ኮሚቴ አባል የነበሩ አንድ ሰው መጥፋታቸውንና የደረሱበት እንደማይታወቅም እየተነገረ ነው፡፡

ቀራቅር ላይ ሰልፍ የወጡት ነዋሪዎች “እየደረሰብን ነው” ያሉት “ማዋከብና እሥራት ይቁም” ሲሉ ከተማይቱ ውስጥ በመዘዋወር መጠየቃቸውን አንድ የከተማዪቱ ነዋሪና በሰልፉም ላይ ተገኝቻለሁ ያሉ ሰው ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ሊላይ ብርሃኔ የሚባሉ የወልቃይት ኮሚቴ አባል ሰሞኑን ከጎንደር ወደ ዳንሻ እየተመለሱ ሳሉ መንገድ ላይ መጥፋታቸው በአካባቢው አነጋጋሪ እየሆነ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ከጎንደር ወደ ሁመራ የሚወስደውን መንገድ የሃገሬው ሰው በኮረትና በእንጨት ስለዘጋው መመላለስ እንደማይቻል አንድ የሶሮቃ ከተማ ነዋሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ከአካባቢው ባለሥልጣናት መረጃ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሣካም፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የወልቃይት ኮሚቴ አባል ጠፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:41 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG