በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ.ተ. መ.ድ. 3ኛ ኮሚቴ በኤርትራ ውስጥ ስለሚገኘው የሰብአዊ መብት ሁኔታ ሪፖርቱን አቀረበ


ሺላ ኪታሩት (Sheila B. Keetharuthe)
ሺላ ኪታሩት (Sheila B. Keetharuthe)

የ.ተ. መ.ድ. 3ኛ ኮሚቴ በኤርትራ ውስጥ ስለሚገኘው የሰብአዊ መብት ሁኔታ ሪፖርት አድምጧል። ሪፓርቱን በተመለከተ በመንግሥታቱ ድርጅት የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮም መልስ ሰጥተዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ማንዴታቸውንና ኃላፊነታቸውን እአአ ባለፈው ሐምሌ 2015 እንዳደሰላቸው የገለጹት ልዩ ራፖርቷሯ በመግቢያቸው፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በኤትራው የምርመራ ኰሚሽን ውስጥ የሊቀ-መንበርነት ቦታቸው እንደተጠበቀ መሆኑን አመልክተው፣ "በዛሬ ሪፖርቴ" አሉ፣ «ከማነሳቸው ዋና ዋና ስጋቶች መካከል፣ እአአ ባለፈው ሰኔ 2015 ለጠቅላላ ጉባዔው ያቀረብኳቸው ነጥቦች ተካተውባቸዋል» ብለዋል።

እነዚህም የኤክኖሚ፣ የባህልና የማኅበራዊ ነፃነቶች፣ ህገ-ወጥ የሰዎች መናገድና በየወሩ ከ5,000 በላይ ከሚሆኑ ከአገር ከሚሸሹ ጋር አብረው የሚወጡ ህፃናትን ጉዳይ ይመለከታል ያሉት ሺላ ኪታሩት (Sheila B. Keetharuthe፲, በቅድሚያ ግን ኤሪትራን "አሻሽያለሁ" ያለችውን የህግና የፍርድ ቤት ሥርዓቶችን ጠቅሰዋል። እንዲሁም፣ በህፃናት ጉዳይና በሴቶች መብት ይዞታ ላይ ኤሪትራ በመሳተፏ የሚያስመሰግናት እንደሆነም አልሸሸጉም።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅትየኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮም

ይሁንና ኤሪትራ በጥበቃ ወይም በእስር ላይ የሚፈጸምን ሰቆቃ በተመለከተ እአአ ለጥቅምት 24 ማቅረብ የነበረበት ዘገባ ባለመቅረቡ ያንን እንድታደርግ አበረታታለሁ ብለዋል ሺላ ኪታሩት። ሺላ ኪታሩት ቀደም ሲል ስለጠቀሱት የህፃናት መብት ጉዳይም በዚሁ ሪፖርታቸው ጠቅሰው፣ በምሳሌነትም፣ እዚያ ከኤሪትራ ውስጥ ከ፭ ዓመታት በፊት የታገቱ የሁለት ህፃናትን ታሪክ አንስተዋል።

"ጥያቄ ማቅረብ ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ እነሆ ሁለት ዓመት ወሰደ" የሚሉትሺላ ኪታ ሩት, "ለመሆኑ የኤሪትራ መንግሥት ምን ዘዴ ወይም መፍትዄ አገኘ?" ብለው ይጠይቃሉ።

በመንግሥታቱ ድርጅት የኤሪትራው አምባሳደር አቶ ግርማ አስመሮም ለዚህ ሪፖርት እዚያው መልስ ሰጥተዋል። "ይህ ዘገባ የተዛባ ብቻ ሳይሆን፣ የፖለቲካ ሚክናት ያለውና በተለይም በስፍራው ያልነበረ ሰው ያቀረበው በመሆኑ፣ ያን በማስተባበል ጊዜያችሁን ላጠፋ አልሻም"፣ ሪፖርቱ በመሠረቱ ሙያዊ እውነታን ያልያዘ፣ ገለልተኝነትም የጎደለው ነው ብለዋል።

"የቀረበው ዘገባ፣ ከአሁን ቀደም ሌሎች የተመድ ወኪሎችና ዲፕሎማቶች ያቀረቧቸውን፣ ሊረጋገጡም የሚችሉ ሪፖርቶችን የሚቃረን ነው" ብለዋል አምባሣደር ግርማ አስመሮም።

ሺላ ኪታሩት ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ተመርኩዘን ሰፋ ያለ ዝግጅት ለማቅረብ ባቀድንው መሠረት ቀጠሮ ተቀብለናል፣ ለማቅረብ እንሞክራለን። የዛሬን ሙሉ ዝርዝር ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የ.ተ. መ.ድ. 3ኛ ኮሚቴ በኤርትራ ውስጥ ስለሚገኘው የሰብአዊ መብት ሁኔታ ሪፖርት አድምጧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:39 0:00

ከዚህ በታች ያለው ቪድዮ በመጫን የኮሚቴውን ሪፖርት ይመልከቱ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኤርትራ ውስጥ ስለሚገኘው የሰብአዊ መብት ሁኔታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:28:39 0:00

በተጨማሪም የዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ለኤርትራ ስደተኞች ጥገኝነት እንዲሰጥ የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዶ ነበር።

ዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ለኤርትራ ስደተኞች ጥገኝነት እንዲሰጥ የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፍ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:45 0:00

XS
SM
MD
LG