በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤርትራና ኢትዮጵያ የወቅቱና የወደፊት ግንኙነት ጉባዔ ተካሄደ


ኤርትራና ኢትዮጵያ
ኤርትራና ኢትዮጵያ

ጉባዔውን በጋራ ያዘጋጁት፥ ቪዝን ኢትዮጵያ (Vision Ethiopia) እና ኢሳት (ESAT)ናቸው።

ቪዝን ኢትዮጵያ (Vision Ethiopia) የተሰኘ፥ ነዋሪነታቸው በዩናይትድ ስቴትስ የሆነ የኢትዮጵያውያን ምሁራንና ባለሞያዎች ነፃ ስብስብ፥ ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን /ኢሳት/ ጋር በመተባበር ”የኢትዮጵያና ኤርትራ ወቅታዊና የወደፊት ግንኙነት” በሚል ርዕስ ያዘጋጁት ሰፊ የውይይት መርሃ ግብር በቅርቡ እዚህ በዋሺንግተን ዲ ሲ ተካሂዷል።

ባለፈው ሳምንት ፕሮግራማችን፥ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የኢትዮጵያና የኤርትራ ማህበረሰብ መሪዎች ያላቸው ሚና በሚለው ርዕስ የአራት አስረጂዎችን አስተያየቶች ባጫጭሩ ሰምተናል።

ዛሬ የኃያላን መንግሥታትና ያካባቢው ኃይሎች በአፍሪካ ቀንድ ያላቸው ፍላጎት ምንድነው የሚለውንና፥ በኤርትራ መንግሥትና በኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች መካከል ያለው ግንኙነት የሚለውን እናያለን።

በኤርትራና ኢትዮጵያ የወቅቱና የወደፊት ግንኙነት ጉባዔ ተካሄደ

አስረጂዎች ቀድሞ በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሀርማን ኮሀን (Herman Cohen) እና የቀድሞው የኢትዮጵያ ዲፕሎማት አምባሳደር ዶክተር ካሣ ከበደ ናቸው።

ሰሎሞን ክፍሌ በሥፍራው ተገኝቶ ያቀናረው ዘገባ አለ። ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኤርትራና ኢትዮጵያ የወቅቱና የወደፊት ግንኙነት ጉባዔ ተካሄደ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:32 0:00

XS
SM
MD
LG